Детальная рекламная статистика будет доступна после прохождения простой процедуры регистрации
: 15'772 | на пост: 569 | ER: 4.3% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-21 11:18:49 |
570
0 |
"በእውነቱ የዚህ ታሪካዊ:ሃይማኖታዊና ጥበባዊ በአእምሮ ልህቀት የሰውን ልጅ ራሱ አእምሮውን በዚህ ብሩህ ጎዳና እንዲመራ የጥንቱን የኢትዮጵያ ነገር ከአሁኑ ጋር አዋህዶ እያሰላሰለ:በምክንያታዊ መሳጭ ጭብጦች እንደ እንዝርት የሚሽከረከር የትንሳኤችን መነሻና መድረሻ መጽሐፍ በመተረኬ ታላቅ ኩራትና ደስታ ይሰማኛል።
"ድራጎን በኢትዮጵያ ሰማይ " ሰው ርዕሱን አይቶ ሰው በትክክል አውሬ ድራጎን ይጠብቃል። የብዙ ሰወች አጻጻፍ ርዕሱ አይቶ የሚገመት መጽሐፍ ነው የሚጽፉት።
እዚህ ርዕስ ውስጥ ከርዕሱ ተቃራኒ ብቻ ሳይሆን ያልገመትናቸው በርካታ ሀሳቦች ታጭቀዋል።
አንድ የተረዳሁት እውነት ደራሲው ርዕስ ሲሰጥ ያመነበትንና የራሱን መንገድ ተከትሎ መጓዝ መቻሉ ነው።
ለአዲስ ትውልድ የተጻፈ ገጸ በረከት ብየዋለሁ።
ጋዜጠኛና ተራኪ ተሾመ ሽፈራው::
: 15'772 | на пост: 569 | ER: 4.3% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-14 09:26:44 |
774
0 |
“ሰው የቱን ነው? አንድ ሰው ማንን ነኝ ብሎ ነው መናገር የሚችለው?
የመረጠውን? እርሱ ብቻ የፈለገውን? ወይንስ ሰው ሁሉንም ነው? የኖረውን
ግብስብስ ሁሉ? ከሆነስ የትኛው ነው ልኩ? በእርግጥ ሕይወት አንድ ቀን
አይደለችም። የአንድ ቀን ውሎም አይደለችም። ትላንት ዛሬና ወደፊት ያላት
ናት። ታዲያ ሁሉንም እንዴት በአንዴ መሆን ይቻላል? ማን በድፍረት ‘እኔ
ይህን ነኝ’ ብሎ ስለራሱ ይናገራል? ‘ክፉ ሰው፣ መልካም ሰው’ ሊባል
የሚችል ሰው ዓለም ላይ አለ?”
ፓርታ፥ ገጽ 194
በቅጡ አልተዋወቅንም። የወረስነው አንዳች ነገር ሳይኖር ‘ወራሾች’ ግን ተብለናል። ሞት ሞት ሆኖ አልተሰጠንም። ሞትን ግን ሞት ያደረግነው እኛው ነን። በሌሎች ውስጥ ራሳችንን አልሆንም። ከመለስነው ዓለም ይልቅ ያልመለስነው ይበዛል። መቼ እና እንዴት ጎዶሎነታችን እንደሚያበቃ እንጃ። መሆን ግን አልነበረበትም። ...ሞታችን ሞት የሆነው በነጠላነታችን፣ በጎዶሎነታችን፣ ባለመደገማችን ውስጥ ነው። የሐሳብና የዕውቀት ተነጥሎ ነው። ለብቻችን፣ ተደብቀን ያደረግነው ይበዛል። ለብቻችን ተደብቀን ያሰብነው ብዙ ነው። የሐሳባችን ጎተራ ምስጢራዊ ነው። የተጋራነው ሕልም የለም። ይህ ሞታችንን ሞት አድርጎታል።
ፓርታ፥ ገጽ 190