Детальная рекламная статистика будет доступна после прохождения простой процедуры регистрации
: 15'819 | на пост: 0 | ER: 4.3% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-14 09:26:44 |
734
0 |
“ሰው የቱን ነው? አንድ ሰው ማንን ነኝ ብሎ ነው መናገር የሚችለው?
የመረጠውን? እርሱ ብቻ የፈለገውን? ወይንስ ሰው ሁሉንም ነው? የኖረውን
ግብስብስ ሁሉ? ከሆነስ የትኛው ነው ልኩ? በእርግጥ ሕይወት አንድ ቀን
አይደለችም። የአንድ ቀን ውሎም አይደለችም። ትላንት ዛሬና ወደፊት ያላት
ናት። ታዲያ ሁሉንም እንዴት በአንዴ መሆን ይቻላል? ማን በድፍረት ‘እኔ
ይህን ነኝ’ ብሎ ስለራሱ ይናገራል? ‘ክፉ ሰው፣ መልካም ሰው’ ሊባል
የሚችል ሰው ዓለም ላይ አለ?”
ፓርታ፥ ገጽ 194
በቅጡ አልተዋወቅንም። የወረስነው አንዳች ነገር ሳይኖር ‘ወራሾች’ ግን ተብለናል። ሞት ሞት ሆኖ አልተሰጠንም። ሞትን ግን ሞት ያደረግነው እኛው ነን። በሌሎች ውስጥ ራሳችንን አልሆንም። ከመለስነው ዓለም ይልቅ ያልመለስነው ይበዛል። መቼ እና እንዴት ጎዶሎነታችን እንደሚያበቃ እንጃ። መሆን ግን አልነበረበትም። ...ሞታችን ሞት የሆነው በነጠላነታችን፣ በጎዶሎነታችን፣ ባለመደገማችን ውስጥ ነው። የሐሳብና የዕውቀት ተነጥሎ ነው። ለብቻችን፣ ተደብቀን ያደረግነው ይበዛል። ለብቻችን ተደብቀን ያሰብነው ብዙ ነው። የሐሳባችን ጎተራ ምስጢራዊ ነው። የተጋራነው ሕልም የለም። ይህ ሞታችንን ሞት አድርጎታል።
ፓርታ፥ ገጽ 190