Телеграм канал 'የፀጋ ወንጌል'

የፀጋ ወንጌል


505 подписчиков
99 просмотров на пост

📌በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች ይለቀቃሉ
📌ጥያቄዎች ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር ይመለሳሉ
📌የእናንተ ድርሻ Share በማድረግ ሰው የእውነትን ወንጌል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ ነው

Group
https://t.me/Graceofjesushighpriestgroup

ሀሳብ እና አስተያየት +251985406785(@yabsen)
+251953843618(@josi1423)
✍የጌታን ፀጋ ይብዛላቹህ

Детальная рекламная статистика будет доступна после прохождения простой процедуры регистрации


Что это дает?
  • Детальная аналитика 5'853'190 каналов
  • Доступ к 1'533'798'153 рекламных постов
  • Поиск по 5'706'775'512 постам
  • Отдача с каждой купленной рекламы
  • Графики динамики изменения показателей канала
  • Где и как размещался канал
  • Детальная статистика по подпискам и отпискам
Telemetr.me

Telemetr.me Подписаться

Аналитика телеграм-каналов - обновления инструмента, новости рынка.

Найдено 93 поста

❤️#ዳግም_ስለተወለድን_ማመን_ችለናል❤️
==================================
✍️ ይህ አስተምህሮ በቀደመችው ቤተክርስቲያን የደህንነት ቅደም ተከተል (ordo salutis) በሚል ትምህርት ውስጥ የሚገኝ ፣የሚታወቅና የሚታመን በግልጥም ትምህርቱ የሚሰጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ነው። ነገር ግን በዚህ ዘመን እየተረሳ ያለ አስተምህሮ ነው።ይህ አስተምህሮ ሉአላዊ የሆነው አምላክ በሀጥያት ለተበላሸውና ሙት ለሆነው ሰው ዳግም ልደትን በመስጠት ማመንና ወደ ብርሃን አለም መቀላቀል የሚችልበትን እውነት የሚያስረዳ አስተምህሮ ነው።
✍️ዳግም ልደት መንፈስ ቅዱስ ወደ ሰው መንፈስ በመምጣት ለሰው መንፈስ የአምላክን ሕይወት በማካፈል ሕያው የሚያደርግበት መለኮታዊ አሰራር ነው።በመቀጠልም ከታደሰ የሰው ልብ ውስጥ የሚወጣ መልካም ምላሽ እምነት ይሆናል።
✍️ ሐዋርያው ጳውሎስ ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁም እንዳለ
አንድ ሰው ከወላጆቹ ለመወለድና በዚህ ምድር ላይ ህይወትን ተካፍሎ ለመኖር የሚያደርገው ነገር ምንድነው? ወላጆቻችንን የምናውቃቸውም ሆነ የምናምናቸው ከተወለድን በኃላ እንጂ ገና ሳንወለድ በፊት አይደለም። በክርስቶስ ለማመንም ሆነ የእግዚአብሔርን መንግስት እንድንቀላቀል መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን የዳግም ልደትንና ህይወት የምናገኝበትን ስራ ይሰራል።
📌 ይህ የሚሆነው ለምንድነው?
------------------------
ኃጢአተኛ የሆነ ሰው ከእግዚአብሔር ሕይወት የተለየ፣ በበደሉና በኃጢአቱ የሞተ፣ ለመንፈሳዊ ነገር ሀሳቡ የታወረ ፣ የእግዚአብሔር ጠላት፣ የሰይጣንና የዓለምን ፈቃድ የሚፈጽም ፣ መንፈሳዊ ነገር ሞኝነት የሆነበት ስለሆነ። በዚህም ምክንያት ሀጥያተኛና በመንፈሱ ሙት የሆነ ሰው በመንፈስ ቅዱስ በኩል ወደ እርሱ የመጣውን ወንጌል ለመቀበልና ለማመን በራሱ አይችልም።ነገር ግን ለኃጢአተኛው ሰው ወንጌል በሚሰበክበት ሰዓት መንፈስ ቅዱስ ህያውነትን ይሰጠዋል ያም ሰው ማስተዋልና ማመን የሚችልበትን አቅም ያገኛል በማመንም ለወንጌል ምላሽን ይሰጣል።
📌 ሮሜ 3፡10-17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦
¹¹ ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፤ ሁሉ ተሳስተዋል፥
¹² በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ ቸርነት የሚያደርግ የለም፥ አንድ ስንኳ የለም።
¹³ ጕሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፥ በመላሳቸውም ሸንግለዋል፤ የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለ፤
¹⁴ አፋቸውም እርግማንና መራርነት ሞልቶበታል፤
¹⁵ እግሮቻቸው ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው፤
¹⁶ ጥፋትና ጉስቁልና በመንገዳቸው ይገኛል፥
¹⁷-¹⁸ የሰላምንም መንገድ አያውቁም። በዓይኖቻቸው ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም።
✍️ በዚህ በሮሜ 3:10-18 ባለው ክፍል ሁለንተናው በኃጥያት የተበላሸውን ሀጥያተኛ ሰው ያሳየናል። ሀጥያተኛው ሰው እግዚአብሔርን ስለፈለገ አይደለም ምክንያቱም ቃሉ እግዚአብሔርን የሚፈልግ የለም ይላል። እግዚአብሔር ግን እኛን ማዳን ስለፈለገ አንድያ ልጁን ልኮልናል። ስለመረጥነው ሳይሆን ስለመረጠን መዳን ሆኖልናል።
✍️ የእግዚአብሔር ቃል ጕሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው....አፋቸውም እርግማንና መራርነት ሞልቶበታል ይላል። ታድያ ከዚህ ሰው ውስጥ ምን አይነት የመዳን ተስፋና እምነት ይገኛል። ይህ ሰው በራሱ እግዚአብሔርን ማመንና መምረጥ ስለማይችል የእግዚአብሔር መንፈስ አሰራር ያስፈልገዋል ስለዚህም መንፈስ ቅዱስ ዳግም እንዲወለድ በማድረግ ማመን የሚችልበትን አቅም ይሰጠዋል።
📌 ያዕቆብ 1 (James)
18፤ ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።
✍️ አንድ ሰው በስጋ ልደቱ አስቦበት እንደማይወለድ ሁሉ ሀጥያተኛም ሰው አስቦበት ሳይሆን እግዚአብሔር አስቦ እንደወለደው ይናገራል።
በዚህ ጥቅስ ውስጥ አምነን ተወለድን ሳይሆን እግዚአብሔር በእውነት ቃል አስቦ ወለደን ይላል። እግዚአብሔር ከወለደን እምነት ደግሞ የዳግም ልደት ውጤት ይሆናል።
📌 ኤፌሶን 2 (Ephesians)
1-2፤ በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው።
3፤ በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን።
✍️ እነዚህ ጥቅሶች ዳግም ልደትን ያላገኘ በመንፈሱ ሙት የሆነውን ኃጥያተኛ ሰው የሚያሳዩ ሲሆን። ይህ ሰው በአየር ላይ ለሚገዛው በሰይጣን ፈቃድ የተያዘና የቁጣ ልጅም ስለሆነ እግዚአብሔርን ለማመን እና ወደ እግዚአብሔር ለመምጣት በራሱ አይችልም። ለዚህም የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አሰራር ያስፈልገዋል።
📌 1 ቆሮንቶስ 2 (1 Corinthians)
14፤ ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።
✍️ በዚህ ጥቅስ ውስጥ የምንማረው እውነት ፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔርን መንፈስ ነገር አይቀበልም ለሱ ሞኝነት ነው ሊረዳቸው አይችልም።
📌 ዮሐንስ 6 (John)
37፤ አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፥ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፤
✍️ በዚህ ጥቅስ መሰረት በኃጥያቱ ሙት የሆነ ሰው በራሱ ብቃት ወደ ኢየሱስ መምጣት እንደማይችል እንመለከታለን። ኃጥያተኛ ሰው ወደ ኢየሱስ ለመምጣት የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት ያስፈልገዋል ስለዚህም ኢየሱስ አብ የሚሰጠኝ ካለ እኛ ራሳችንን ለኢየሱስ መስጠት አንችልም ማለት ነው።
📌 “የላከኝ አብ ካልሳበው በቀር ማንም ወደ እኔ መምጣት አይችልም
— ዮሐንስ 6፥44 (አዲሱ መ.ት)
✍️ በዚህ ጥቅስ ውስጥ ኢየሱስ ሀይማኖተኛ ሰዎች ሲያንጎራጉሩ የመለሰው መልስ ነው።አባቴ ካልሳበው በቀር ሲል በኢየሱስ ማመንና ወደ ኢየሱስ መምጣት የምንችለው ከእግዚአብሔር ዘንድ በእኛ ውስጥ የሚፈጸም አንዳች መለኮታዊ እርዳታ ሲኖር ብቻና ብቻ ነው።
📌 ኤፌሶን 2 (Ephesians)
5፤ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥
✍️ በበደሉና በሀጥያቱ ምክንያት በመንፈሱ ሙት የሆነ ሀጥያተኛ ሰው ከብርሃን ይልቅ ጨለማን የሚመርጥ ስለሆነ ለብርሃን አለም በራሱ ብቃት መልስ መስጠት የማይችል ነው።ስለዚህ ለዚህ ሙት ሀጥያተኛ ሰው እመን ሳይሆን የሚባለው ህይወት ነው የሚያስፈልገው ምክንያቱም ከሞተ ሰው የሚወጣ ትክክለኛ እምነት አይኖርም ለዛም ነው እግዚአብሔር ከልጁ ጋር አስቀድሞ ህይወትን የሚሰጠው። ይህ ህይወት ያገኘው ሰው ህይወትን ባገኘበት ቅጽበት ማመን የሚችልበትን አቅም ያገኛል ከታደሰው ልቡም የሚወጣ ትክክለኛ እምነት ይሆናል።
2 ቆሮንቶስ 13 (2 Corinthians)
14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
https://t.me/Graceofjesushighpriest https://t.me/Graceofjesushighpriest


Найдено 93 поста