Телеграм канал 'በክርስቶስ ( in christ)'

በክርስቶስ ( in christ)


676 подписчиков
111 просмотров на пост

Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin

Детальная рекламная статистика будет доступна после прохождения простой процедуры регистрации


Что это дает?
  • Детальная аналитика 5'783'942 каналов
  • Доступ к 1'533'798'153 рекламных постов
  • Поиск по 5'123'649'962 постам
  • Отдача с каждой купленной рекламы
  • Графики динамики изменения показателей канала
  • Где и как размещался канал
  • Детальная статистика по подпискам и отпискам
Telemetr.me

Telemetr.me Подписаться

Аналитика телеграм-каналов - обновления инструмента, новости рынка.

Найдено 559 постов

(ክርስቶስ በየትኛው ልብ ውስጥ የሚኖረው ?)


#በክርስቶስ ደም በተረጨ ልብ ውስጥ

#በመንፈስ ቅዱስ በኩል የእግዚአብሔር ፍቅር በፈሰሰበት ልብ ውስጥ

#የእግዚአብሔር ታላቅ ምህረት ያረፈበት ልብ ውስጥ

#ክርስቶስ ኢየሱስ ይመጣል በሚል ግሩም ተስፋ በተሞላ ልብ ውስጥ

#በእግዚአብሔር የህልውና መአዛ በታወደ ፤ በታጠነ ልብ ውስጥ

#ኢየሱስ የሚለውን ስም ሁልጊዜ እንዲጠራ ፈቃድ በሰጠው ልብ ውስጥ

#ክርስቶስ ኢየሱስ  በራሱ ለራሱ በዋጀው ልብ ውስጥ


        ክርስቶስ ኢየሱስ የሚኖርበት ልብ ራሱ ክርስቶስ ባፈሰሰው ደም የደመቀ፣ በቅዱስ መንፈሱ የተዋበ፣ በጥልቅ ፍቅሩ ያሸበረቀ ፣ በድንቅ ስሙ ያበራ፣ በአስደናቂው ፀጋ የተጥለቀለቀ፣ በተባረከው ተስፋ ኢየሱስ በኩል የታወደ፣ ውድ በሆነው ምህረቱ የሚያብረቀርቅ ልብ ውስጥ ክርስቶስ ይኖረናል ።

     " ኢየሱስ ሌላ ምንም አላለንም ደም ባፈሰስኩበት ልብ ውስጥ ልኑር "

@cgfsd
@ownkin

❤ 7
👍 1
😢 1
Изображение

ዛሬ በዙዎች በተራሮች፣ በትልልቅ አብያተ ክርስቲያናት፣ በድንጋይ እና በፍሬም ህንፃዎች ይሰግዳሉ። ኢየሱስ ግን መዳን በእነዚህ የድንጋይ ሕንጻዎች ውስጥ እንዳልሆነ ያስተምራል በተራሮች ላይ አይደለም በተራሮች ላይ አይደለም ነገር ግን በእግዚአብሔር ነው የዳነ እና የተቀደሰ ማንኛውም ሰው የኢየሱስን ስም ሲጠራ በልቡ ውስጥ እሳት ሲነድ ይሰማዋል። በህይወታችን በእያንዳንዱ ጊዜ የኢየሱስ ክርስቶስን ደም እናክብር፣ እናም በነፍሳችን ጣፋጭ እንሆናለን።

ዊሊያም ጄ ሲሞር

@cgfsd

❤ 14

(ጌታ ኢየሱስ )



አንዳንድ ቀኖች የየራሳቸው መለያ አላቸው ። ሐሙስ የቀን ንጉስ ብለን ዘክረናል ፣ አርብ ከኋላ ላሉት 2 የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናቶች እንደ ማጣፈጫ ቅመም  ቆጥረናል ። የዛሬ አንድ አመት በፊት የአርብ ፕሮግራም (friday service) ለመካፈል ረፈድፈድ አድርጌ ነበር የወጣሁት ። ጓደኞቼን ዛሬ ብዙ ሰው አለ ቦታ እንዳይሞላብህ  ይዘንልሃል አርፍደሃል ትንሽ ከቆየህ ጥሩ ቦታ አታገኝም እያሉ ሜሴጅ በተደጋጋሚ ላኩልኝ ። እንደደረስኩ የተያዘልኝ ቦታ ወደ መጨረሻ አካባቢ ነበር ፤ ከፊት ለፊቴ መድረኩን ስመለከት በግማሽ ምሶሶ ይጋርደኛል ምቾት ባይሰጠኝም ምንም ምርጫ ስላልነበረኝ በግማሽ መድረኩን አያለሁ በሚል ተስፋ ተደላድዬ ተቀመጥኩ ።

የአምልኮ ጊዜ አለቀ ። ወደ መጨረሻ ስለተቀምጥኩ ወደ ፊት አካባቢ ጨለም ብሎ ነበር የሚታየኝ ። የዕለቱ ፕሮግራም መሪ ዛሬ ቃል የሚያስተምረን  ጋሽ አብዱ ናቸው ብሎ ተናገረ በሩቅ ስላለሁ ይሁን ማይክ ስላልተጠቀመ ብዙ ንግግሩ አልተሰማኝም ። ብቻ ፕሮግራም መሪው ከተናገረ በኋላ አስተማሪው እየሮጠ ማለት በሚቻል መልኩ ከመድረኩ ስር ተንበርክኮ ጌታ ኢየሱስ ፣ ጌታ ኢየሱስ ፣ ጌታ ኢየሱስ ፣ ጌታ ኢየሱስ ፣ ጌታ ኢየሱስ ፣ ጌታ ኢየሱስ እያሉ በተደጋጋሚ ይጣራሉ ፤ ከተንበረከኩበት አንገታቸው ብቻ ብቅ ሲያረጉ ፂማቸው ሂና የተቀቡ ሙስሊም የሚመስሉ ሰው ናቸው ። ጉባኤ ፊታቸውን ሲያይ ይሔ ሙስሊም ሰውዬ ምን ያህል ቢነካ የሚል አስተያየት ሳያያቸው አይቀርም ። ጉባኤው በሞላ አብረን በአንድነት በእንባ ጌታ ኢየሱስ እያልን ከልብ ስሙን ጠራን ።  ያስተማሩት ትምህርት አንጀት ቢያርስም የማረሳው ግን በተደጋጋሚ የተናገሩት ብዙ ጊዜ ይሔን ኢየሱስ የሚለውን ስም የመጥራት ልማድ የለንም !! በቻላችሁት መጠን ልክ ጥሩት ፣ ከሚያስደንቁ ልምምዶች  መካከል ዋነኛው ስሙን በቻላችሁት መጠን ከመረዳት ጋር ፣ ከመወደድ ጋር ፣ ከልብ ከሆነ ፍላጎት ፣ በስሙ ውስጥ ያለው መንፈሳዊ ሚስጥር ከመረዳት በመጀመር ኢየሱስ የሚለውን ስም  መጥራት ።

ከወር በኋላ የወንድሜን የህክምና ውጤት ዶክተር አረዳኝ ። እንዲሁ በቀላሉ ካንሰር ሲል የሰማሁትን እውነት መቋቋም አልቻልኩም ። ወንድሜ ሳያየኝ በዛው ሆስፒታል በመታጠቢያ ክፍል ውስጥ ረጅም ደቂቃዎች አለቀስኩ ። በቀላሉ የምቋቋመው አልነበረም ከቤተሰብ ተለይቼ የዛኑ ቀን ወደ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ነው የማድረው በማለት በእግሬ ረጅም መንገድ ሄድኩ ። መንገድ ላይ ለመፀለይ ሞከርኩ አልቻልኩም ። ለመጮኸ መኮርኩ አልቻልኩ ፣ ለማውራት ሰው ፈለኩ የቅርቤ የምላቸው እንኳን የሌለኝ መሰለኝ  ።

በመንገድ ላይ እያለሁ ከወር በፊት በጉባኤው ውስጥ ጌታ ኢየሱስ ብለን ከልብ በሆነ ናፍቆት ቅዱስ ስሙን የጠራንበት ጊዜ ትዝ አለኝ ። ከዛም እንዲህ እያልኩ መንገድ ላይ መፀለይ ጀመርኩ
  "የራሴ ድምፅ ብዙ ጊዜ ረበሽኝ ፣ እኔነቴ ያለ ቅጥ  መፈናፋኛ አሳጣኝ ፣ ድካሜ ጉልበቴን ለግሞ ያዘኝ ፣ የምሰማው ነገር አስደነገጥ  በዚህ ሁሉ ግን ስምህ መማፀኛ ግንብ ሆነኝ ። በዙሪያ ካሉት ሁሉ ዘልዮ አመለጥኩበት ። ቃላት አጥቼ ጌታ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ እያለኩ ለማምለጥ ጠራሁት ነገር ግን ማምለጡን ረስቼ የጠራሁት ስምህ ጣፈጠኝ ጌታ ኢየሱስ ብዬ ሳልጨርስ ከእንደገና ስሙን መጥራት ናፈቀኝ ። ጌታ ኢየሱስ ስለው የተወጋው ጎኑ ትውስ ይላል፣ጌታ ኢየሱስ ስለው የፈሰሰው ደሙ እንደ ወንዝ ጅረት በአይነ ህሊናዬ እልፍ ይላል፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው በመስቀል እንደ ተንጠለጠ ወድሃለው ሲለኝ ይሰማኛል ፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው ልክ በሌለው ጭንቀቴ ውስጥ ልክ የሌለው ሰላሙ ይፈሳል፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው ሀዘን ጥላውን ባጠላብኝ ነፍሴ ውስጥ ደስታው እንደ ማለዳ ፀሀይ ይፈነጥቅብኛል ፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው በውስጤ ያለው ቅዱሱ መንፈስ ደግሜ እንድጠራው ጉልበት ይሆነኛል ።  ሰሞኑን ብዙ ተጨነኩ ፣ ብዙ አዘንኩ ፣ብዙ አነባሁ ፣ ብዙ ተልፈሰፈስኩ እና ብዙ ብዙ ልል አስቤ ልፀልይ ተንበረከኩ ጌታ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ብዬ ስጣራ በአንድ ቃል ብዙ ተነፈስኩ ፣ አረፍኩ ፣ እፎይይ አልኩ !! "

       ጌታ ኢየሱስ😍



✍ ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd

🔥 11
🥰 9
❤ 4

በመፀሀፍ ቅዱስ ውስጥ የጠፋውን ልጅ ታሪክ ስናነብ በጣም የሚደንቀን የጠፋውን ልጅ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው የአባቱ ልብ ነው ። የአባትነትን ልብ ያየንበት ግሩም ታሪክ ነው ። ነገር ግን አባትዬው እጅግ ደስ የሚለው ጉዳይ ቤት ያለው ያልጠፋው ልጅ አለመጥፋት ብቻ ሳይሆን የጠፋውን ልጅን ያልጠፋው ልጅ አፈላልጎ እንዲያገኝ እና ወደ አባቱ ቤት እንዲመለስ አባቱ በብርቱ ይፈልጋል ። ቤት ያለው ልጅ የአባቱን ልብ አላገኘም ነበር ፤ ቤት ተቀምጦ ከአባቱ ልብ ርቋል ። ኢየሱስ ግን ከዙፋን ፣ ከሰማይ ድረስ የአባቱን ልብ ተረድቶ በበረት ተኝቶ ፣ በሰው መንደር አድጎ ፣ በመስቀል ላይ ውሎ ፣ በመቃብር ውስጥ አድሮ የጠፋውን የሰው ልጅ ፈልጎ አፈላልጎ አገኘ ። የአባት ልብ መረዳት እንዴት ደስ ይላል !! በኢየሱስ በኩል የተገለጠ የአብ ልብ አለ ። የአብን የልብ ሀሳብ ለመረዳት የፈለገ ማንም ቢኖር የአብን ልብ ባረካው በኢየሱስ በኩል ይገኛል ።  አብ በልጁ ኢየሱስ የልቡ ስለደረሰ እሱን ስሙት ብሎ የልብ የልቡን በኢየሱስ በኩል ተናግሯል ። 

@cgfsd
@ownkin

❤ 22
👏 2
🔥 1

መውደዱ በሥጋው መቈረስ ደመቀ፤ ለእኛ ያለው ፍቅሩ በደሙ መፍሰስ ታተመ። በቍስሉ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ተጨባበጥን። በሰማይ ለእግዚአብሔር ክብር፥ በምድር ለሰው ልጅ ሥምረት ኾነ (ሉቃ. 2፥14)። እነሆ፥ ዐዲስ የወዳጅነት መንገድ ተከፈተ። ከእግዚአብሔርም ጋር ኾነ ከሰው ጋር እንታረቅ ዘንድ መድኀኒት በቀራንዮ ተቈረሰ። ድኅነት ታወጀ። ኀጢአት ተሰረየ፤ የቀደመች ኀጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ተተወች፤ ዐመፃ ተጨረሰ፤ የዘላለም ጽድቅ ገባ፤ ምሕረት ተበሠረ፤ ፍቅር በመስቀል ላይ ሠመረ። በትንሣኤው ኀይል ጨለማ ድል ተነሣ፤ ለእግዚአብሔር ክብር ለሰውም ሰላም ኾነ።

                     ሰሎሞን አበበ ገብመድኅን

@cgfsd
@ownkin

🥰 11
🔥 2

#በእስጢፋኖስ ህይወት ውስጥ ያለ የህይወት ጥራት (life quality) ለቅዱሳት መፀሀፍት (መፀሀፍ ቅዱስ) የሚሰጠው ቦታ ትልቅ ነበር። የእግዚአብሔር ሀሳብን ለመርመር በመጀመሪያ የሚከፍተው ቅዱሳት መፀሀፍት ነው ።

* እግዚአብሔር ምን ሰራ በቅዱሱ መፀሀፍት ውስጥ ይመለከታል (ሐዋ 7)

* እግዚአብሔር አሁን ምን እየሰራ እንደሆነ በቅዱስ መፀሀፍት በኩል ይረዳል(ሐዋ7)

* እግዚአብሔር ወደፊት ምን እንደሚሰራ በመፀሀፍ ቅዱስ በኩል ይመረምራል (ሐዋ7)

@cgfsd
@ownkin

❤ 14
🔥 1

#በእስጢፋኖስ ህይወት ውስጥ ያለ የህይወት ጥራት (life quality) ኢየሱስ መምሰል ነበር ።

* እንደ ኢየሱስ ኖረ ( ሐዋ 6 እና 7)
* እንደ ኢየሱስ አገለገለ ( ሐዋ 6እና 7)
* እንደ ኢየሱስ ሞተ (ሐዋ 7:58)

@cgfsd
@ownkin

❤ 17
🥰 1

#በእስጢፋኖስ ህይወት ውስጥ ያለው
የህይወት ጥራት (life quality)በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ነበር ።

* አገልግሎቱን የጀመረው በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት ነበር (ሐዋ 6:5) ።

* አገልግሎቱን የቀጠለው በመንፈስ ቅዱስ እየተሞላ ነበር (ሐዋ 6:8)

* አገልግሎቱን የጨረሰው በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ነበር (ሐዋ 7:54)

   #በመንፈስ ቅዱስ መሞላት በክርስቶስ ላለ ሰው የሚመራበት ሰማያዊ የሆነ የህይወት ስርአት ነው ። 


@cgfsd
@ownkin

❤ 22
🔥 3

እግዚአብሔር በአዲሱ ኪዳን ፀሎታችን ቀምቶናል ። በውስጣችን ከገባው ቅዱስ መንፈስ የተነሳ ፀሎታችን የሚመራው በመንፈሱ በኩል ነው ። እንዴት መፀለይ እንዳለብን እንኳን አናቅም መንፈስ ቅዱስ ግን ያስቃትተናል ፤ እንድንፀልይ ያደረገናል።  እግዚአብሔር በፀሎታችን እንዳንመካ ፀሎታችን ውስጥ ገባ ይሔው በመንፈስ ቅዱስ በመሆን የሚፀለይ ፀሎት ነው ።

@cgfsd
@ownkin

🔥 11
❤ 2

#ፀሎተኛው ኢየሱስ
(ክፍል 2)


ኢየሱስ አስደናቂ የፀሎት ህይወት እንዳለው መፀሀፍ ቅዱሳችን ውስጥ የምናገኘው የተገለጠ እውነት ነው ። ጌታችን ኢየሱስ የፀሎት ህይወት እና ልማዱ ቢያስደንቀንም ከዛ ባልተናነሰ መልኩ የሚፀልይባቸው ጉዳዮችም ያስደንቃሉ ። ኢየሱስ የፀለየባቸው  ርዕሶች በራሳቸው ወይ ጉድ የሚያሰኙ ናቸው ።  ከመድሃኒታችን የምንማረው የፀሎት ህይወት ብቻ ሳይሆን የምንፀልይበትንም ርዕስ ፣ ሀሳብ ፣ ትኩረት መስጠት ያሉብንም ጉዳዮች ነው ።

በተለይም ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን ፀሎት አስተምረን ሲሉት ያስተማራቸው እንዲህ በማለት ነበር " በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ ስምህ ይቀደስ " የሚል ነበር ። በሰማይ የሚኖረውን አባት ስሙ እንዲቀደስ መፀለይ  የኢየሱስ የፀሎት ርዕስ ነበር ። ስምህ ይቀደስ ማለት ስምህ ይለይ ፣ ስምህ ይታወቅ ፣ የስምህ ዝና ይውጣ ፣ በሁሉ ስፍራ አንተ ተወራ፣ ክብር መነጋገሪያ ይሁን እንደማለት ነው ። የኢየሱስ የፀሎት ትኩረት የእግዚአብሔር ክብር እንደነበረ ለደቀመዛሙርቶቹ በትምህርቱ አይተናል ።

ብዙውን ጊዜ ክርስቲያኖች ከምንቸገርባቸው ነገሮች መካከል የመጀመሪያ የምንቆይባቸው የፀሎት የትኩረት ሀሳቦች የሉንም ። እግዚአብሔር በመፀለያችን የሚደሰተውን ያክል በምንፀልይባቸው ጉዳዮችም ይደሰታል ። ከእግዚአብሔር ጋር ያለን እውነተኛ ህብረት መለማመድ ከምንችልባቸው መንገዶች የመጀመሪያን ፀሎት ሲሆን የበለጠ ደግሞ የምንፀልይባቸው ሀሳቦች ከእግዚአብሔር ጋር ምን ያህል ህብረት እንዳለን እንደተረዳን ያሳያሉ ። ኢየሱስ በፀሎቱ የእግዚአብሔር ክብር የስሙ መታወቅ ላይ ትኩረት አደረገ ። በክርስቶስ ያመንን አማኞች እንደመሆናች መጠን የኢየሱስ ትኩረት ያደረገባችው የትኩረት ስፍራዎች ይመለከተናል ። ይባስ ብሎ በውስጣችን የተቀበልነው ቅዱሱ መንፈስ በምን ጉዳይ ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለብን ፣ መቃተት እንደሚኖርብን ፣ ምን የእግዚአብሔር አንገብጋቢ ሀሳብ እንዳለ ያሳስበናል ።


@cgfsd
@ownkin

❤ 6
🔥 1

የፈሰሰውን ፀጋ ፣ የፈሰሰውን ፍቅር፣የፈሰሰውን ደም እንድንረዳ እና እንድናጣጥም የፈሰሰልን መንፈስ አለ!

@cgfsd
@ownkin

🥰 18

እንኳንም የእግዚአብሔርን መንግስት ኢየሱስ አስተዋወቀን !! ንጉሱ ኢየሱስ ወርዶ መንግስቱን በመካከላችን አደረገ ፣ በር ሁኖ የመንግስቱን ሚስጥር ከፈተ ፣ ሞቶ በሁሉ ቦታ መንግስቱን አደረሰ ፣በንግስናው በርካቶችን የንጉሱ ካህናት አድርጎ ሾመ ።

@cgfsd
@ownkin

🥰 18
❤ 3

ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ደጋግሞ ስለ ራሱ፣ ስለ አባቱ ፣ ስለ መንግስቱ ፣ ስለ ተልዕኮው ፣ ስለ ቤተክርስቲያን ብዙ ነገረን ፤ በሞቱ እና በትንሳኤው ደግሞ እጅግ ከፍ ባለ በጩኸት ልናስተባብለው በማንችልበት ልክ አወራን ።

@cgfsd
@ownkin

❤ 11
🔥 3

ኢየሱስ የተዋረደበት እና የከበረበት ልክ  ለማወቅ መንፈስ ቅዱስ በእኛ መካከል የሚኖርበትን አላማ መረዳት አስፈላጊ ነው ። ሰይጣን ወደ ምድር  የወረደው በትዕቢቱ ምክኒያት ተጥሎ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ግን  ወደ ቤተክርስቲያን የመጣበት ምክኒያት የክርስቶስ መክበር ነበር ። መንፈስ ቅዱስ ወደ ቤተክርስቲያን የወረደበት ልክ ኢየሱስ በሰማያት ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያለበት መክበር ነው ። መንፈስ ቅዱስ በቤተክርስቲያን ውስጥ በሀይል ሲንቀሳቀስ ፣ በወንጌል ብዙዎች ሲማረኩ፣ ብዙዎች ከአጋንነት እስራት ነፃ ሲወጡ ፣ በሽተኞች ሲፈወሱ ፣ ቅዱሳን እርስ በእርሳቸው ሲተናነፁ ፣ በህልውና ውስጥ እግዚአብሔርን እየናፈቁ ፣እየፈሩ ፣ በቅድስና መኖርን መንፈስ ቅዱስ በሀይል ሲሰራ የምናስተውለው እውነት ክርስቶስ ምን ያህል በሰማያት  በክብር በግርማ እንዳለ ያሳያል ።

  #በውስጣችን ያለው መንፈስ ቅዱስ አይቀልብንም ፤ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ በመኖሩ በሰማይ ምን እየተከናወለ እንዳለ አውቀናል በዛም ክርስቶስ ከፍ ከፍ ብሎ ያለ ልክ ከብሯል ።



@cgfsd
@ownkin

❤ 18
🥰 3

መስቀሉ ላይ ያየነው ዘላለማዊ ፍቅር መስቀሉ ላይ ብቻ አላበቃም በትንሳኤውም ቀጥሏል ። ኢየሱስ አባቱን እንደሚወደደው  እስከ መስቀል ድረስ በመታዘዝ ጥልቅ ፍቅሩን እንደገለጠ ሁሉ አብም ኢየሱስን እንደሚወደው ኢየሱስን ከሙታን በማስነሳቱ መውደዱን አረጋግጦልናል ። መስቀሉን አይተን በፍቅሩ እንደተደነቅን ሁሉ ትንሳኤውንም እያየን በፍቅሩ እንገረማለን ።

@cgfsd
@ownkin

❤ 13
👍 6

#የክርስቶስ_ግርፋት
#በምሁሩ_ዕይታ
#ክፍል_1

የወዙ እንደ ደም ነጠብጣብ መሆን፥ ይሄ ሁኔታ በህክምናው ዓለም ሄማትድራሲስ በመባል ይታወቃል። ብዙም የተለመደ አይደለም፤ ነገር ግን ከፍተኛ ከሆነ ሥነልቦናዊ ጫና ጋር የሚያያዝ ሁኔታ ነው።

ከባድ ወይም ከመጠን ያለፈ ጭንቀት ላብ እንዲመነጭ በሚያደርጉ እጢዎች ውስጥ የሚገኙትን ደም ስሮች የሚጎዱ ኬሚካሎች እንዲረጩ ያደርጋል። በዚህም በእነዚህ እጢዎች ውስጥ ጥቂት የደም መፍሰስ ይፈጠራል። ስለዚህ ከሰውነት የሚወጣው ላብ ከደም ጋር የተዋሃደ ይሆናል። ይህም ሲሆን ብዙ የደም መፍሰስ ይኖራል ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ጥቂት ደም ከላብ ተቀላቅሎ ይገኛል።

ይህ ክስተት የሰውነት ቆዳን ስስና ደካማ ያደርገዋል፤ ኢየሱስም በቀጣዩ ቀን በሮማውያን ሲገረፍ የሰውነቱ ቆዳ እጅግ ደካማ ሆኖ ነበር። የሮማውያን ግርፊያ እጅግ ጭካኔ የተሞላበት እንደሆነ ይታወቃል። ተለምዷዊው ግርፋት 39 ግርፋት ያህል ነው። ብዙውን ጊዜ ግን ከዚህም ሊበልጥ ይችላል፤ በተለይም ደግሞ ገራፊው ወታደር እንዳለበት ሙድ ወይም ስሜት ሊለዋወጥ ይችላል።

አንድ የሮማ ወታደር ለግርፊያ የሚጠቀመው ጅራፍ ከቆዳ የተሰፋ እና ትንንሽ የማይባሉ የብረት ኳሶች የታሰረበት ጅራፍ ነው። አንዱ ግርፋት ሰውነት ላይ ሲያርፍ እነዚህ የብረት ኳሶች ጥልቅ ቁስል እና ጉዳት ያመጣሉ፤ በኋላም ግርፋቱ ሲደጋገም ከቁስለት ያልፍና የሰውነት ቆዳ እየተከፈ ይሄዳል። ጅራፉ የአጥንት ስብርባሪዎች ጭምር አብሮ የተሰፋበት ሲሆን፥ በሚዘገንን ሁኔታ የሰውነትን ቆዳ ይጎዳሉ።

ይህ ግርፋት የሚደርስበት ሰው ጀርባ፥ ግርፋቱን ተከትሎ ከሚፈጠሩት ትልልቅ ክፍተቶች የተነሳ ሊቦጫጨቅ የሚችል በመሆኑ የጀርባ አጥንት የተወሰነው ክፍል ሳይቀር ሊታይ የሚችልበት አጋጣሚ ይፈጠራል። ግርፋቱ ከትከሻ አንስቶ እስከ ታችኛው ጀርባ፥ አልፎም መቀመጫን እና የእግር ታፋ ጀርባን ሳያስቀር ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል። እጅግ አሰቃቂ ነው።

የሮማውያንንን ግርፍያ ያጠና አንድ ፊሲሺያን "ግርፋቱ እየቀጠለ ሲሄድ፥የቁስሎቹ መቀደድ ወደታችኛው የአጥንት ጡንቻ ድረስ በመዝለቅ እንደደም የሚፈስ የተቦጫጨቀ ሥጋን ይፈጥራል።

ዩሴቢየስ የተባለ በሶስተኛው ክፍለዘመን የነበረ አንድ የታሪክ ምሁር የግርፋቱን ሁኔታ ሲያስረዳ "ይህ መከራ የሚደርስበት ሰው ደም ሥሮቹ፥ ጡንቻዎቹ፥ ጅማቶቹ እና አንጀቱ ሳይቀር ከግርፋቱ የተነሳ ለዕይታ ተጋላጭ ይሆናሉ።

ተገርፈው እንዲሰቀሉ ታልፈው የሚሰጡ ብዙዎቹ ፍርደኞች መስቀሉ ጋር ሳይደርሱ ከግርፋቱ የተነሳ ብቻ ሟቾች ናቸው። በመጨረሻም የሚገረፈው ሰው በቃላት ሊገለፅ ከሚችለው በላይ የሆነ ሕመምን በማስተናገድ ወደ ሃይፖቮለሚክ ሁኔታ ይገባል።

ሃይፖ ማለት "ትንሽ" ሲሆን ቮል (ቮልዩም) ማለት "መጠን" ወይም "ይዞታ" ማለት ነው፤ ኢሚክ ማለትም "ደም" ማለት ነው። ስለዚህ የሃይፖቮለሚክ ሁኔታ ብዙ የደም መፍሰስ የገጠመውን ሰው የሚያመላክት ሁኔታ ነው።

ይሄም ሁኔታ አራት ነገሮችን ይፈጥራል።
አንደኛ፦ ብዙ ደም ቢፈስም የደም ዝውውሩን ለማስቀጠል የልብ ምት በፍጥነት እየጨመረ ይሄዳል።
ሁለተኛ፦ የደም ግፊት ይወርዳል። ይህን ተከትሎ ራስን ስቶ መውደቅ ይፈጠራል።
ሶስተኛ፦ ኩላሊቶች የፈሳሽ ማጣራት ስራን መስራት ያቆማሉ። ይህም በብዙ ደም መፍሰስ ምክንያት ብዙ ፈሳሽ ከሰውነት ስለወጣ ተጨማሪ ፈሳሽ እንዳይወጣ ለማድረግ ነው።
አራተኛ፦ ሰውነት በደም መፍሰስ ምክንያት ያጣውን ፈሳሽ ለመተካት ከፍተኛ የሆነ የውሃ ጥማት ይፈጠራል።

ኢየሱስም አንደኛውን የመስቀሉን ክፍል ተሸክሞ ወደ ቀራንዮ በሚወጣበት ጊዜ በሃይፖቮለሚክ ሁኔታ ውስጥ ገብቶ ነበር። በመጨረሻም ኢየሱስ ራሱን ስቶ በመውደቁ የሮማው ወታደር ስምኦንን መስቀሉን እንዲሸከምለት አዘዘው። በኋላ ላይም ኢየሱስ "ተጠማው" ሲል እና ወይን ሲሰጠው እናነባለን።

ግርፋቱ ካደረሰበት ከባድ ጉዳት የተነሳም ኢየሱስ ገና የሚሰቀልባቸው ሚስማሮች በእጆቹ እና በእግሮቹ ከመቸንከራቸው አስቀድሞ እጅግ አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ ሊሆን እንደሚችል ምንም ጥያቄ የለውም።

ዘ ኬዝ ፎር ክራይስት (The Case for Christ)፥ 1998 እ.አ.አ
ሊ ስትሮቤል ከ ዶ/ር አሌክሳንደር ሜዜሬል ጋር ካደረገው ቃለምልልስ የተወሰደ
ለዚህ ልጥፍ እንዲመች ተደርጎ የተዘጋጀ
ከገፅ 194-196

በጌታ በኢየሱስ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው!!!

✍Kdus zewdu

@cgfsd

❤ 6

በክርስቶስ ኢየሱስ ትንሳኤ ያገኘናቸው በረከቶች ምን ምን ናቸው ?

@cgfsd
@ownkin

🔥 3
🥰 1

ትንሳኤ ኢየሱስ ተፈፀመ  ብሎ ለተናገረው ንግግር አብ አሜን ያለበት ነው ።

Art Azurdia

@cgfsd
@ownkin

❤ 9
🤔 2
👍 1
🔥 1

እግዚአብሔር ለእኛ ባደረገው የደም ኪዳን ታማኝ መሆኑን ያረጋገጥነው በክርስቶስ ትንሳኤ ነው ። እግዚአብሔር በክርስቶስ የተሰራው የመስቀል ስራ ለዘላለም የሚሆን አስተማማኝ እንደሆነ ያሳየን በክርስቶስ ትንሳኤው በኩል አረጋግጦልን ነው ።

@ownkin
@cgfsd

❤ 13
🥰 2

Найдено 559 постов