(የክርስቶስ እርገት)
በክርስትና ውስጥ ክርስቶስን በተመለከተ የክርስቶስ ውልደት ፣ ሞት ፣ ትንሳኤና ዳግም መምጣት አስፈለጊ እንደሆነ ዋና የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነበት መጠን የክርስቶስ እርገት እጅግ ወሳኝና አስፈላጊ ነው ።
እንዲህም አሏቸው፤ “እናንት የገሊላ ሰዎች ሆይ፤ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ እዚህ የቆማችሁት ለምንድን ነው? ይህ ከእናንተ ዘንድ ወደ ሰማይ ሲያርግ ያያችሁት ኢየሱስ፣ ልክ ወደ ሰማይ ሲወጣ እንዳያችሁት በዚሁ ሁኔታ ይመለሳል።”
ሐዋርያት ሥራ 1:11
የክርስቶስ ማረግ በረከቶች
1, በክርስቶስ የተሰራው ስራ (ሞቱና ትንሳኤው) እውነት መሆኑን ያረጋግጥልናል።
2, የክርስቶስ ምልጃ ሊቀ ካህናዊ አገልግሎት እንደሚቀጥል ዋስትና ይሆነናል ።
3, ዳግም ተመልሶ እንደሚመጣ የማይነቃነቅ ፅኑ ተስፋ ይሆንልናል ።
4, በስጋ በማረጉ አሁንም የሰው ዘመድ ወገን ለሰው ተቆርቆሪ እንደሆነ ገብቶን እምነትና መደገፍን ይጨምርናል ።
5, በአዲሱ የትንሳኤ አካል በመነሳቱና በማረጉ በአዲሱ የትንሳኤ አካል በትንሳኤ ቀን እንደምንነሳ ማረጋገጫችን ይሆንልናል ።
6, እኔ ብሄድ ይሻላችኋል ያለው እሱ በመሆኑ ፤ በክርስቶስ እርገት ምክኒያት መንፈስ ቅዱስ እኛ መካከል እያፅናናን እንዲሰራ አድርጎልናል ።
7, ክርስቶስ በማረጉና በመክበሩ ወደ ፀጋው ዙፋን በድፍረት የመግባት ነፃነት ተቀናጅተናል ።
የክርስቶስ እርገት የክርስትና ውበታችን እጅግ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ። እንደ ሞቱና ትንሳኤው እርገቱም ዋና ነው ።