Каталог каналов Новое Каналы в закладках Мои каналы Поиск постов
Инструменты
Мониторинг Новое Детальная статистика Анализ аудитории Telegraph-статьи Бот аналитики
Полезная информация
Инструкция Telemetr Документация к API Чат Telemetr
Полезные сервисы
Защита от накрутки Создать своего бота Продать/Купить канал Монетизация

Прикрепить Телеграм-аккаунт Прикрепить Телеграм-аккаунт

Телеграм канал «በክርስቶስ ( in christ)»

በክርስቶስ ( in christ)
736
340
3
0
8.1K
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Подписчики
Всего
1 258
Сегодня
0
Просмотров на пост
Всего
310
ER
Общий
20.77%
Суточный
13.6%
Динамика публикаций
Telemetr - сервис глубокой аналитики
телеграм-каналов
Получите подробную информацию о каждом канале
Отберите самые эффективные каналы для
рекламных размещений, по приросту подписчиков,
ER, количеству просмотров на пост и другим метрикам
Анализируйте рекламные посты
и креативы
Узнайте какие посты лучше сработали,
а какие хуже, даже если их давно удалили
Оценивайте эффективность тематики и контента
Узнайте, какую тематику лучше не рекламировать
на канале, а какая зайдет на ура
Попробовать бесплатно
Показано 7 из 736 постов
Смотреть все посты
Пост от 15.09.2025 09:42
156
0
1
አይ ወንጌል !! ቀኑ በአንድ ትንፋሽ እንደተጨለጠ ውሃ ቶሎ ያለቀ ይመስላል ። ወደ ከተማው ስንገባ መሸትሸት ስለሚል አይን ያዝ ያደርጋል ። ረጅም ስለተጓዝን ሰውነታችን ስብርብር ብሏል ። የት እንደምናድር እያሰብን አንድ ቦታ እንፈልጋለን እየተባባል እያለ ፤ ሲመራን የነበረው ሰው ወዳጆቹን እስቲ ልጠይቃቸው ብሎ ይዞን ገባ ። የገባንበት ጎጆ ባልና ሚስት ልጆቻቸው ከተማ ስለገቡ ብቻቸውን ነው የሚኖሩት ። ስንገባ አባወራው በደስታ ተቀበለን ሰው ሊጠይቀን መጣ ማለት ነው በማለት ፈነደቀ ። ገና ወደ ውስጥ ሳንገባ ሊቀበለን ሹር ጉድ ማለት ጀመረ ። ሚስቱ አሟት ተኝታ ነበር ። እሷም እንግዳ እንደመጣ ስትሰማ ህመሟን ረስታ በደስታ ለማስተናገድ በፈገግታ ተነሳች ። እየተሳሳቁ በደስታ እስክንጨነቅ ድረስ አስተናገዱን ። ፊታቸው ላይ ያለው ደስታ በደንብ ያስታውቃል ምክኒያቱ ግን ምንድን ነው? እያልን እየተገረምን እርስ በእርሳችን ተነጋገርን ። በኋላ ደፈር ብለን ጠየቅናቸው ። ምንድን ነው? እንዲህ እንግዳ እንድትወዱ ያደረጋችሁ የአካባቢው ባህል ነው ? ወይስ ሌላ ምክኒያታችሁ ምንድን ነው ? ፈገግ እንዳለ አባወራው እንዲህ አለን " የትውልድ መንደሬ እዚህ አልነበረም በወንጌል ስደት የተነሳው ከብዙ አመታት በፊት ነው እዚህ የመጣነው ። በወቅቱ በምኖርበት መንደር እኔና ባለቤቴ ብቻ ነበርን አማኝ ። እኛ ብቻ የወንጌል አማኝ ስለሆን ሁሉም ሰው ይጠላናል ። ቤታችን የሚመጣ አንድም ሰው የለም። ሰላም ያለን ይወገዛል ። የገዛ ቤተሰቦቼ ለአይን ተፀየፉኝ ። አንድ ቀን የሰባት አመት ሴት ልጃችን ከፍተኛ ትኩሳት ያዛት ከ2 ቀን በኋላ ከሌሊቱ ስምንት ሰአት ገደማ አረፈች ። በሰአቱ ብዙ ሰው ስሌለን አዘንን። ከቤት ወጥቼ ጎረቤት አካባቢ ወንድሜን ጠራሁት ፣ የመንደር ሰዎች ጠርቼ ወደ ቤት ተመለስኩ፤ ብጠብቅ ብጠብቅ ዝር የሚል አንድም ሰው የለም ። ቆይታ እናቴ መጣች እሷም ምንም ሳትል በውስጧ አልቅሳ 5 ደቂቃ ሳትቆይ ጥላ ሄደች ። እኔና ባለቤቴ በሃዘን ተቆራምተን ቁጭ አለን ። ባለቤቴ ቀጥላ እንዴ ምንድን ነው? የምትጠብቀው ማን እንዲመጣ ነው ? ሰው ባይኖረን ጌታ እኮ አለን አለችኝ ። ወዲያውኑ ልቤ በረታ ። ልጃችን ለሁለት ገነዝናት በራሳችን በቅጥር ግቢያችን ውስጥ ቀበርናት "።  ያኔ በወንጌል ምክኒያት አንድ ሰው እንኳን አልነበረንም ቤታችን የሚገባ  ፤ አሁን ታዲያ በወንጌል በኩል ሰው ሲገባ ተገኝቶ ነው ። እንግዳ ስጠን ብለን ፀልየን እናውቃለን ።በወንጌል ጠያቂ ሰው አጥተን ስለምናቅ በወንጌል ጠያቂ ስናገኝ ክብር ነው " አለን በፈገግታ እንደተሞላ ። አብሮኝ ያለው ወንጌላዊ ይሔ ሲሰማ ድምፅን ከፍ አድርጎ " አይ ወንጌል " አለ አባወራውም ተከትሎ በደስታ" እውነትም አይ ወንጌል" አለ ተከትሎት ። @cgfsd
🥰 5
🔥 3
1
Пост от 13.09.2025 21:34
244
0
0
Изображение
2
Пост от 12.09.2025 14:46
304
0
0
Изображение
20
Пост от 11.09.2025 17:47
344
0
0
አይ ወንጌል ! 1980ዎቹ አጋማሽ  ብዙ መረጋጋት በሀገሪቱ በማይስተዋልበት አካባቢ ማፌድ በሚባል መንደር አንድ የክርስቲያን ቤተሰብ ልጅ ከዚህ አለም በሞት ይለያል ። በስፍራው በጣት የሚቆጠሩ የወንጌል አማኞቾ ብቻ ስላሉ ብዙ ስደት ውስጥ እንደ ቤተሰብም እንደ ሀገርም እያለፉ ነበር። ልጁ ያረፈባቸው ቤተሰቦች ልጁን የሚቀብሩበት የቀብር ቦታ ያጣሉ ፤ የማህበረሰቡን ሽማግሌ ቢለምኑ ምን ሊተባበራቸው የሚችል አንድ ሰው ሊያገኙ አልቻሉም ። የቀብር ቦታ ስሌላቸው ራቀ አርገው እንዲቀብሩ አንድ ቦታ ጠቆሟቸው  ። በተባለው ቦታ ልጁን ጥቂት አማኞች አዝነው ቀብረው ተመለሱ ። በነጋታው ከዋዳ የተባለ ቦታ ጥቂቶች አማኝ የነበሩ ወጣቶች በለቅሶ ሀዘን ያለውን ቤተሰብ ተሰናብተው የ4 ሰአት መንገድ ተጉዘው በስንት እድል የተገኘውን ኮንፈራን ለመካፈል ይሄዳሉ ።  በሰአቱ ተግኝተው ፕሮግራም እየተካፈሉ እያለ ፤ ከመሃከላቸውን ወጣቶችን ያስተባብር የነበረው ወንድም በዝማሬ መሃል በተቃራኒ አቅጣጫ ሲመለከት የልጁ አባት አይኖቹ እንባ አዝለው ተመለከተ ። በድንጋጤ የ4ሰአት መንገድ አቋርጦ ከሀዘን ተነስቶ የመጣው ምን ሁኖ ነው በማለት ግራ እየተጋባ ወደ ውጮ ይዞት በመውጣት አናገረው ። አባትዬውም  እያለቀሰ ሳናቅ ያኔ መቃብር ስናጣ ልጄ የተቀበረበት መሬት ዙሪያው የጅብ ጉድጓድ መኖሪያ ነው ። የልጄን አስክሬን ከተቀበረበት ጅቦቹ አውጥተው በሉት ። አሁን የተቀረው የተቆራረጠ ሰውነት ክፍሉና አጥንቱ ብቻ ነው ። በሰአቱ የወጣቶቹ አስተባባሪ እንዲህ ይለናል " ተቃቅፈን እያለቀስን ወደ ስፍራው ለመመለስ ተነሳን ። በወቅቱ ኮንፈራንስ እያገለገለ የነበረው ፓስተር ዘማሪ ታምራት ሃይሌ ነበሩ ። ይሔን ታሪክ ሲሰሙ ኮንፈራንሱን ትቼ አብሬ ይሔ ልጅ በክብር ቀብራለው ብለው የአራት ሰአቱን መንገድ ኮንፈራንሱን ትተው አብረውን መጡ ።  የጅብ ጎድጓድ አጠገብ የተበተነውን የልጁን አጥንት ሰብስበን ወደ ቤት ተመለስን ። ድጋሜ ከቦታ አንፃር መቅብር ስላልተቻለ ፓስተር ዘማሪ ታምራት ሃይሌ አፅናንተውን ተመለሱ ። ይሔ ሲፈጠር አንድ ቶማስ የተባሉ አገልጋይ ። ይሔን ሲሰሙ የልጁን አጥንት በሰሌን ጠቅልለው ወደ ወደ አዲስ አባባ መጡ ። ከአንዳንድ ሰዎች ጋር በመሆን በወቅቱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ታምራት ላይኔ ጋር ገቡ ። በለቅሶ ህዝቡ የተቸገረ እንደሆነ ቤቱ ግቢ ውስጥ እየቀበረ እየኖረ እንዳለ የያዙትም አጥንት በጅብ ከተቀበረበት የተበላ እንደሆነ አስረዱ ። ጠቅላይ ሚኒስተሩ ቦታ እንዲሰጣቸው በደብዳቤ ፅፎ ሸኛቸው። ወደ ትውልድ መንደራቸው ሲመጡ የተሰጣቸውን ደብዳቤ ቢሰጡ ሰሚ ያጣሉ ። መልስ እስኪያገኙ መቅበሪያ ቦታ ስልነበራቸው ፤ በቤታቸው ቆጥ ላይ በሰሌኔን የጠቀለሉትን አጥንት ሰቀሉት ።  መንደርተኛው መቀበሪያ እንኳን የሌላችሁ እምነት ይላቸው  ነበር ። ከ9ወር በኋላ ቦታ ተሰጣቸው ከቤታቸው ቆጥ አውርደው የልጁም ቤተሰብ ተፅናንቶ በዝማሬ ጌታን አመስግነው ቀበሩ" ። ይሔን ታሪክ ያኔ ወጣቶች ሲያስተባብር የነበረው ወንድምና በቤታቸው 9ወር ያስቀመጡት አገልጋይ ጋር  በተነካ ልብ ትውስታ ለእኔና ለወንጌላዊው አጋሩን ። ይሔኔ አብሮኝ የነበረው ወንጌላዊ እየደጋገመ " አይ ወንጌል ፣ አይ ወንጌል  ..ከጅብ ጉድጓድ ያስቀብራል ፣ በሃዘን የ4 ሰአት መንገድ ያስጉዛልም ፣ ኮንፈራንስ ሰርዞ ላፅናና ያስብላልም ፣ 9ወር በቤት መቅበሪያ ቦታ ታጥቶ አጥንት በቤት ያሰቅላል ፣ ደግሞ በራሱ ጊዜ በዚሁ ሁሉ መከራ ያበረታልም ፣ ሀይል ይሆናል ፣ ራሱ ወንጌሉ ብዙዎች ማርኮ ካሳ ይሆናል ። አይ ወንጌል " @cgfsd
9
🔥 4
Пост от 07.09.2025 19:03
431
0
3
(አይ ወንጌል ) በሌሊት አይሱዙ ቅጥቅጥ ተሳፍሬ ወደ አንድ ገጠር አካባቢ ተጓዝኩ ። የሚቀበለኝ ወንጌላዊ  ጋር ተገናኘን ። ቦርሳዬን ተቀብሎ እያወራን መራመድ ጀመርን ። በመሃል ዝቅ ሲል ያረኩት ቶርሺን ጫማ አይቶ ፈገግ አለ ። "አሁን ይሔ ጫማ እዚህ ያዛልቃል ብለህ ነው ? ባይሆን ቦቲ እንገዛለን" አለኝ ። በተራዬ እሱ ያደረገውን ቦቲ ጫማ እያየሁ ፈገግ አልኩኝ ። እንዳለው ከተወሰነ በኋላ ጭቃውና የሳሩን ርዝመት ልቋቋመው አልቻልኩም ። አሁንም ማወራት ቀጠልን እዚህ ድረስ መጣህ አይደል እዚህ ገጠር አለኝ " እየተገረመ ። አዎን በሚመስል መልኩ ጭንቅላቴን ነቀነቁለት እሱም ቀጥሎ  " አይ ወንጌል "  የማይሰራው የለም እዚህ ድረስ አምነህ መምጣት ወንጌል እኮ ነው ። አይ ወንጌል! ማረፊያችን የነበረው በቸርች ግቢ ውስጥ ስለነበር ገብተን የተወሰነ እንዳረፍን ። አሁንም የመሃሉ "ወይ ጉድ አይ ወንጌል ይሔ አደረገ ይላል ። ወንጌላዊው በእድሜ ለእኔ አባቴ ይሆናል ። ስለ አስተዳደጉና ስለ አገልግሎቱ አጫወተኝ ።  አሁን የምታየው የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው የተወለድኩት ነገር ግን ከዚህ ወጥቼ አዲስ አበባ ከገባሁ 30 አመት አልፎኛል ። አሁን ተመልሼ እዚሁ ሚሽነሪ ሁኜ ከመጣሁ ደግሞ ገና 4ወሬ ነው ። እኔም በተራዬ እየተገረምኩ  አዲስ አበባ ልጆችህን ፣ ባለቤትህ ፣ የልጅ ልጆችና ቤተሰብ ካለበት ፤ እዚህ ወደ ገጠር መብራት የለ ፣ ውሃ የለ ፣ ኔትወርክ የለ ፣ ት/ቤት የለ፣ ሆስፒታል የለ ፣ ሱቅ የለ እዚህ ለመኖር መጣኸ አይከብድህም ? አልኩት ። ፈገግ ብሎ  " ምን መሰለህ ወንጌል ነዋ  አይ ወንጌል ! ወንጌል ይሔ አደረገ ። እንደውም ምን መሰለህ የምመኘው ቢሳካልኝ ሩቅ በቃ የማላቀው ቦታ ሩቅ ሂዶ ወንጌል እየሰሩ መኖር ነው ። ለስለስ ባለ መቋጫ ድምፅ " አይ ወንጌል አለ ደግሞ ።" አማኝ የሆኑ በእድሜ ተለቅ ያሉ በአካባቢው የተከበሩ ሰው ቤት ለመክሰስ ተጠራን ሄድን ።  ስንደርስ ከብቶቻቸውን እየጠበቁ ነበር ።  ከብቶቻቸውን ለመጠበቅ ጫማ አላረጉም ። አባባ ጋር ከጎጆ ቤታቸው በረንዳ ላይ ተቀምጠን በትርጉም የተወሰነ አወራን። እሳቸውም " ከአዲስ አባባ ዛሬ መጣህ? አሉኝ " አዎ ብዬ መለስኩላቸው ። እሳቸውም እየተገረሙ ደገሙት " አይ ወንጌል " አሉ ። ወደ ማረፊያችን ከተመለስን በኋላ በአካባቢ ሱቅ ስለሌለ ምግብ ማግኘት አልቻልንም ። እራት ፣ ቁርስ ፣ ምሳ በቆሎ እየተጠበሰ እሱን በላን ። መሃል ላይ አልበላ ሲለን ወንጌላዊ" አይ ወንጌል " ይላል እንደ ማበረታቻ ። ቆየት ይልና የአካባቢው አለመመቸትና ትልሽ ልቡን ያወርደዋል መልሶ ከእንደገና "አይ ወንጌል " እያለ ይደሰታል ። አይ ወንጌል ! የወንጌል አቅም ትልቅ ነው ። ሀጢያተኛን የማፅደቅ ሃይል አለው ። ብዙ ለውጦች አለም ላይ ቢስተዋሉም እውነተኛውና ታላቁ ለውጥ የወንጌል ለውጥ ነው ። ወንጌል የመለወጥ ብቻም ሳይሆን የማኖርም አቅም አለው ። አይ ወንጌል ! የስንቱን ህይወት ለወጠ ስንቱን አንበረከከ ። ከወንጌል የማዳን ፣ የማኖር አቅም ስላለው ነው ፤ ለዚህም ነው ጳውሎስ የወንጌል ማህበርተኛ ለመሆን ስለወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ ያለው (1ቆሮ9)።  አይ ወንጌል ! @cgfsd
14
🔥 6
🥰 1
Пост от 06.09.2025 08:53
384
0
0
Изображение
17
Пост от 04.09.2025 19:15
373
0
0
Изображение
20
🔥 5
Смотреть все посты