Телеграм канал 'በክርስቶስ ( in christ)'

በክርስቶስ ( in christ)


660 подписчиков
98 просмотров на пост

Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin

Детальная рекламная статистика будет доступна после прохождения простой процедуры регистрации


Что это дает?
  • Детальная аналитика 5'622'381 каналов
  • Доступ к 1'533'798'153 рекламных постов
  • Поиск по 4'988'724'192 постам
  • Отдача с каждой купленной рекламы
  • Графики динамики изменения показателей канала
  • Где и как размещался канал
  • Детальная статистика по подпискам и отпискам
Telemetr.me

Telemetr.me Подписаться

Аналитика телеграм-каналов - обновления инструмента, новости рынка.

Найдено 546 постов

ኢየሱስ የተዋረደበት እና የከበረበት ልክ  ለማወቅ መንፈስ ቅዱስ በእኛ መካከል የሚኖርበትን አላማ መረዳት አስፈላጊ ነው ። ሰይጣን ወደ ምድር  የወረደው በትዕቢቱ ምክኒያት ተጥሎ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ግን  ወደ ቤተክርስቲያን የመጣበት ምክኒያት የክርስቶስ መክበር ነበር ። መንፈስ ቅዱስ ወደ ቤተክርስቲያን የወረደበት ልክ ኢየሱስ በሰማያት ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያለበት መክበር ነው ። መንፈስ ቅዱስ በቤተክርስቲያን ውስጥ በሀይል ሲንቀሳቀስ ፣ በወንጌል ብዙዎች ሲማረኩ፣ ብዙዎች ከአጋንነት እስራት ነፃ ሲወጡ ፣ በሽተኞች ሲፈወሱ ፣ ቅዱሳን እርስ በእርሳቸው ሲተናነፁ ፣ በህልውና ውስጥ እግዚአብሔርን እየናፈቁ ፣እየፈሩ ፣ በቅድስና መኖርን መንፈስ ቅዱስ በሀይል ሲሰራ የምናስተውለው እውነት ክርስቶስ ምን ያህል በሰማያት  በክብር በግርማ እንዳለ ያሳያል ።

  #በውስጣችን ያለው መንፈስ ቅዱስ አይቀልብንም ፤ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ በመኖሩ በሰማይ ምን እየተከናወለ እንዳለ አውቀናል በዛም ክርስቶስ ከፍ ከፍ ብሎ ያለ ልክ ከብሯል ።



@cgfsd
@ownkin

❤ 12
🥰 3

መስቀሉ ላይ ያየነው ዘላለማዊ ፍቅር መስቀሉ ላይ ብቻ አላበቃም በትንሳኤውም ቀጥሏል ። ኢየሱስ አባቱን እንደሚወደደው  እስከ መስቀል ድረስ በመታዘዝ ጥልቅ ፍቅሩን እንደገለጠ ሁሉ አብም ኢየሱስን እንደሚወደው ኢየሱስን ከሙታን በማስነሳቱ መውደዱን አረጋግጦልናል ። መስቀሉን አይተን በፍቅሩ እንደተደነቅን ሁሉ ትንሳኤውንም እያየን በፍቅሩ እንገረማለን ።

@cgfsd
@ownkin

❤ 13
👍 6

#የክርስቶስ_ግርፋት
#በምሁሩ_ዕይታ
#ክፍል_1

የወዙ እንደ ደም ነጠብጣብ መሆን፥ ይሄ ሁኔታ በህክምናው ዓለም ሄማትድራሲስ በመባል ይታወቃል። ብዙም የተለመደ አይደለም፤ ነገር ግን ከፍተኛ ከሆነ ሥነልቦናዊ ጫና ጋር የሚያያዝ ሁኔታ ነው።

ከባድ ወይም ከመጠን ያለፈ ጭንቀት ላብ እንዲመነጭ በሚያደርጉ እጢዎች ውስጥ የሚገኙትን ደም ስሮች የሚጎዱ ኬሚካሎች እንዲረጩ ያደርጋል። በዚህም በእነዚህ እጢዎች ውስጥ ጥቂት የደም መፍሰስ ይፈጠራል። ስለዚህ ከሰውነት የሚወጣው ላብ ከደም ጋር የተዋሃደ ይሆናል። ይህም ሲሆን ብዙ የደም መፍሰስ ይኖራል ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ጥቂት ደም ከላብ ተቀላቅሎ ይገኛል።

ይህ ክስተት የሰውነት ቆዳን ስስና ደካማ ያደርገዋል፤ ኢየሱስም በቀጣዩ ቀን በሮማውያን ሲገረፍ የሰውነቱ ቆዳ እጅግ ደካማ ሆኖ ነበር። የሮማውያን ግርፊያ እጅግ ጭካኔ የተሞላበት እንደሆነ ይታወቃል። ተለምዷዊው ግርፋት 39 ግርፋት ያህል ነው። ብዙውን ጊዜ ግን ከዚህም ሊበልጥ ይችላል፤ በተለይም ደግሞ ገራፊው ወታደር እንዳለበት ሙድ ወይም ስሜት ሊለዋወጥ ይችላል።

አንድ የሮማ ወታደር ለግርፊያ የሚጠቀመው ጅራፍ ከቆዳ የተሰፋ እና ትንንሽ የማይባሉ የብረት ኳሶች የታሰረበት ጅራፍ ነው። አንዱ ግርፋት ሰውነት ላይ ሲያርፍ እነዚህ የብረት ኳሶች ጥልቅ ቁስል እና ጉዳት ያመጣሉ፤ በኋላም ግርፋቱ ሲደጋገም ከቁስለት ያልፍና የሰውነት ቆዳ እየተከፈ ይሄዳል። ጅራፉ የአጥንት ስብርባሪዎች ጭምር አብሮ የተሰፋበት ሲሆን፥ በሚዘገንን ሁኔታ የሰውነትን ቆዳ ይጎዳሉ።

ይህ ግርፋት የሚደርስበት ሰው ጀርባ፥ ግርፋቱን ተከትሎ ከሚፈጠሩት ትልልቅ ክፍተቶች የተነሳ ሊቦጫጨቅ የሚችል በመሆኑ የጀርባ አጥንት የተወሰነው ክፍል ሳይቀር ሊታይ የሚችልበት አጋጣሚ ይፈጠራል። ግርፋቱ ከትከሻ አንስቶ እስከ ታችኛው ጀርባ፥ አልፎም መቀመጫን እና የእግር ታፋ ጀርባን ሳያስቀር ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል። እጅግ አሰቃቂ ነው።

የሮማውያንንን ግርፍያ ያጠና አንድ ፊሲሺያን "ግርፋቱ እየቀጠለ ሲሄድ፥የቁስሎቹ መቀደድ ወደታችኛው የአጥንት ጡንቻ ድረስ በመዝለቅ እንደደም የሚፈስ የተቦጫጨቀ ሥጋን ይፈጥራል።

ዩሴቢየስ የተባለ በሶስተኛው ክፍለዘመን የነበረ አንድ የታሪክ ምሁር የግርፋቱን ሁኔታ ሲያስረዳ "ይህ መከራ የሚደርስበት ሰው ደም ሥሮቹ፥ ጡንቻዎቹ፥ ጅማቶቹ እና አንጀቱ ሳይቀር ከግርፋቱ የተነሳ ለዕይታ ተጋላጭ ይሆናሉ።

ተገርፈው እንዲሰቀሉ ታልፈው የሚሰጡ ብዙዎቹ ፍርደኞች መስቀሉ ጋር ሳይደርሱ ከግርፋቱ የተነሳ ብቻ ሟቾች ናቸው። በመጨረሻም የሚገረፈው ሰው በቃላት ሊገለፅ ከሚችለው በላይ የሆነ ሕመምን በማስተናገድ ወደ ሃይፖቮለሚክ ሁኔታ ይገባል።

ሃይፖ ማለት "ትንሽ" ሲሆን ቮል (ቮልዩም) ማለት "መጠን" ወይም "ይዞታ" ማለት ነው፤ ኢሚክ ማለትም "ደም" ማለት ነው። ስለዚህ የሃይፖቮለሚክ ሁኔታ ብዙ የደም መፍሰስ የገጠመውን ሰው የሚያመላክት ሁኔታ ነው።

ይሄም ሁኔታ አራት ነገሮችን ይፈጥራል።
አንደኛ፦ ብዙ ደም ቢፈስም የደም ዝውውሩን ለማስቀጠል የልብ ምት በፍጥነት እየጨመረ ይሄዳል።
ሁለተኛ፦ የደም ግፊት ይወርዳል። ይህን ተከትሎ ራስን ስቶ መውደቅ ይፈጠራል።
ሶስተኛ፦ ኩላሊቶች የፈሳሽ ማጣራት ስራን መስራት ያቆማሉ። ይህም በብዙ ደም መፍሰስ ምክንያት ብዙ ፈሳሽ ከሰውነት ስለወጣ ተጨማሪ ፈሳሽ እንዳይወጣ ለማድረግ ነው።
አራተኛ፦ ሰውነት በደም መፍሰስ ምክንያት ያጣውን ፈሳሽ ለመተካት ከፍተኛ የሆነ የውሃ ጥማት ይፈጠራል።

ኢየሱስም አንደኛውን የመስቀሉን ክፍል ተሸክሞ ወደ ቀራንዮ በሚወጣበት ጊዜ በሃይፖቮለሚክ ሁኔታ ውስጥ ገብቶ ነበር። በመጨረሻም ኢየሱስ ራሱን ስቶ በመውደቁ የሮማው ወታደር ስምኦንን መስቀሉን እንዲሸከምለት አዘዘው። በኋላ ላይም ኢየሱስ "ተጠማው" ሲል እና ወይን ሲሰጠው እናነባለን።

ግርፋቱ ካደረሰበት ከባድ ጉዳት የተነሳም ኢየሱስ ገና የሚሰቀልባቸው ሚስማሮች በእጆቹ እና በእግሮቹ ከመቸንከራቸው አስቀድሞ እጅግ አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ ሊሆን እንደሚችል ምንም ጥያቄ የለውም።

ዘ ኬዝ ፎር ክራይስት (The Case for Christ)፥ 1998 እ.አ.አ
ሊ ስትሮቤል ከ ዶ/ር አሌክሳንደር ሜዜሬል ጋር ካደረገው ቃለምልልስ የተወሰደ
ለዚህ ልጥፍ እንዲመች ተደርጎ የተዘጋጀ
ከገፅ 194-196

በጌታ በኢየሱስ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው!!!

✍Kdus zewdu

@cgfsd

❤ 6

በክርስቶስ ኢየሱስ ትንሳኤ ያገኘናቸው በረከቶች ምን ምን ናቸው ?

@cgfsd
@ownkin

🔥 3
🥰 1

ትንሳኤ ኢየሱስ ተፈፀመ  ብሎ ለተናገረው ንግግር አብ አሜን ያለበት ነው ።

Art Azurdia

@cgfsd
@ownkin

❤ 9
🤔 2
👍 1
🔥 1

እግዚአብሔር ለእኛ ባደረገው የደም ኪዳን ታማኝ መሆኑን ያረጋገጥነው በክርስቶስ ትንሳኤ ነው ። እግዚአብሔር በክርስቶስ የተሰራው የመስቀል ስራ ለዘላለም የሚሆን አስተማማኝ እንደሆነ ያሳየን በክርስቶስ ትንሳኤው በኩል አረጋግጦልን ነው ።

@ownkin
@cgfsd

❤ 13
🥰 2

እግዚአብሔርን የምናውቀው በተገለጠልን ልክ ነው የእግዚአብሔር የመገለጥ ልክ ደግሞ ኢየሱስ ። የብሉይ ኪዳን አባቶች ሳይቀሩ እግዚአብሔር ይረዱት የነበረው በተገለጠላቸው መጠን ነበር ። ለአብርሃም አልሻዳይ፣ ለሙሴ ያህዌ ብሎ በነገራቸው መሰረት ተረዱት ። ነገር ግን ይሔን እግዚአብሔር በትክክል ለመግለጥ ኢየሱስ መገለጡ አስፈላጊ ነው ። ኢየሱስ የመገለጥ ወኪል ነው እግዚአብሔርን የተረዳትበት የመጨረሻ መንገድ እሱ ብቻ ነው ። ኢየሱስ የመጨረሻው የእግዚአብሔር ግልጠት ነው ። እግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን ራሳችንም የምናውቀው በኢየሱስ በኩል በክርስቶስ ኢየሱስ ባገኘነው ማንነት ማንነታችን በኢየሱስ በኩል እናውቃለን ።

@cgfsd
@ownkin

❤ 12
🔥 3

አለም ከተፈጠረ ጀምር እሰከ ዛሬ ድረስ ያልተለወጡ የምንጊዜም የመጨረሻ እጅግ በጣም ድንቃድንቅ እና ትላልቅ ሶስት ተአምራት (the greatest miracle ever)

#የክርስቶስ ሰው መሆን
#የክርስቶስ መሞት
#የክርስቶስ ትንሳኤ

ምን አይነት ተአምር ነው !!
(what a miracle)

@cgfsd
@ownkin

❤ 15
🥰 4

የኢየሱስ የማንነቱ ማረጋገጫ ራሱ ነው ። እርሱ መፅሀፍ አልፃፈም ፣ የሚመራው የጦር ሀይል አልነበረውም ፣ የፖለቲካ ስልጣን አልጨበጠም ፣ ወይም የሀብት ማማን አልተቆናጠጠም ። በምድር ላይ አገልግሎቱ፥ ከኖረበት መንደር በአንድ መቶ ኪሎ ሜትር የርቀት ወሰን ውስጥ ነበር የተመላለሰው ። ነገር ግን ፥ አቻ ያልነበረው ሕይወቱ ፥ልብ ሰርስሮ የሚገባው ትምህርቱና እጅ በአፍ የሚያስጭኑት ስራዎች የሰዎችን ትኩረት ስበው አምነውበት እንዲከተሉት ወይም እንዲቃወሙት ያስገድዱ ነበር ።


የተቆረሱ ነፍሶች

@cgsfd

👍 5
🔥 3

ፀጋ በክርስቶስ ቤዛነት ስራ እንድንመካ 💪 ያደርጋል !! በእርግጥ ፀጋ እንዲሁ በነፃ  ይሰጥ እንጂ "እንዲሁ" እንዲሰጥ ትልቁ ዋጋ ከፍሎ ሂሳባች ያወራረደው ክርስቶስ ነው በቤዛነቱ አማካኝነት ፤ ለእኛ እንዲሁ በነፃ ነው ለክርስቶስ ግን የሞት ዋጋ ፣ ቤዛነት አለበት ። ስለዚህ በክርስቶስ ቤዛነት ዋጋ መክፍል ፀጋው እንዲሁ ስለተሰጠ ! ፀጋው የክርስቶስን የቤዛነት ስራ ያጎላል ፣ ጮክ ብሎ ይናገራል 🗣 ፀጋ ሲነሳ የክርስቶስን ያ ድንቅ የመስቀል ስራ ሁልጊዜ ይነሳል ።




@cgfsd
@ownkin

❤ 12
👍 5

(#ፀሎተኛው ኢየሱስ)



ወዲያውም እርሱ ሕዝቡን እያሰናበተ ሳለ፣ ደቀ መዛሙርቱ በጀልባ ወደ ቤተ ሳይዳ ቀድመውት እንዲሻገሩ አዘዛቸው፤  ከዚያም ትቶአቸው ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።
ማርቆስ 6:45-46

ከእነዚያም ቀናት በአንዱ ኢየሱስ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ።  ሲነጋም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ ከእነርሱ ዐሥራ ሁለቱን መረጠ፤ እነዚህንም ሐዋርያት ብሎ ሰየማቸው፤
ሉቃስ 6:12-13


ኢየሱስ 5ሺ ሰዎች ማለትም ቤተሰባቸው ተጨምሮ ሲቆጠር ከ15ሺ እሰከ 20ሺ የሚሆን ህዝብ አስከትሏል እና አስተምሯል ነገር ግን ካስተማረ በኋላ ሁሉን አሰናብቶ ለብቻው ፈቀቅ ይል ነበር ። የምን ህዝቡን ሰዎች ብቻ የቅርቡ የነበሩትን ደቀመዛሙርቱን ሸኝቶ ለብቻው ሊፀልይ ፈቀቅ ይል ነበር ፤ ለብቻም መፀለይ አስፈላጊ ነው  ።  ቀን ቀን ያገለግላል ሌሊት ሌሊት ይፀልያል ። ብዙዎችን ያስተምራል ለብቻው ይፀልያል ።

ከኢየሱስ የፀሎት ህይወት የተማርነው ነገር ቢኖር ፀሎት ከአባት ጋር የሚኖር ጫፋጭ ህብረት ነው ። ሲፀልይም አባት ሆይ እያለ ከአባቱ ጋር ያለው ግሩም ህብረት በመፀለይ ይኖረዋል ። እጅግ ደስ ሲለው አባቱን በፀሎት ያመሰግነዋል ፣ ሲያዝንም ከእንባ ጋር ይፀልያል ። በደስታውም፣ በሀዘኑም ጊዜ ከአባቱ ጋር በፀሎት ህብረት ያረጋል ። ፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ውድ ህብረት የምናጣጥምበት አንዱ መንገድ ነው ።

ኢየሱስ ሊሰቀል ሲል ከመሰቀሉ አንድ ቀን ቀድሞ በጌተሰማኒ እየፀለየ ነበር ። የመስቀል ሞት ከፊት ተደቅኖበት እሱ ግን ይፀለያል ። ከኢየሱስ ከመስቀሉ አንድ ቀን በፊት በነበረው ፀሎት የምንናስተውለው ነገር ፀሎት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማስቀየሪያ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ፈቃድ መስማሚያ እንደሆነ ነው ፤  ቢቻል  ፈቃድ ከሆነ ይሔ ፅዋ ከእኔ ይለፍ ያንተ ፈቃድ እንጂ የእኔ እይሁን እያለ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር በፀሎቱ መስማማቱን ያሳያል ።
          
ከእነርሱም የድንጋይ ውርወራ ያህል ርቆ ተንበርክኮ ጸለየ፤  እንዲህም አለ፤ “አባት ሆይ፤ ፈቃድህ ከሆነ፣ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይፈጸም።” መልአክም ከሰማይ ተገልጦለት አበረታታው።  እጅግ ተጨንቆም በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም እንደ ደም ነጠብጣብ ወደ ምድር ይፈስ ነበር።
ሉቃስ 22:41-44

ኢየሱስ ሲፀልይ ብዙ ጊዜ ትኩረት የሚደርግበት የፀሎቱ ሀሳብ የእግዚአብሔር  በሰዎች ዘንድ እንዲታወቅ ነበር ። ደቀመዛሙርቱን ፀሎት ሲያስተምራቸው የተናገረው የመጀመሪያው የፀሎቱ ሀሳብ እንደዚህ የሚል ነበር " ስምህ ይቀደስ" ። ስምህ ይቀደስ ማለት ስምህ ይነገር ፣ ስም በህዝቦች መካከል ዝናው ይወጣ ፣ ክብር ለሰዎች ይታወቅ ፣ በሁሉ ቦታ አንተ ታወቅ እንደማለት ነው ። በኢየሱስ ፀሎት ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳት እግዚአብሔር በሰዎች ዘንድ እንዲታወቅ ነበር ።

  አገልግሎት ሊጀምር ሲል 40 ቀን እና አርባ ሌሊት ፣ እያገለገለም አብዝቶ ይፀልይ ነበር ። መስቀል ላይ ተሰቅሎ እንኳን 3 ፀሎቶችን ፀለየ እነርሱም :- የሚያደርጉት አያቁም እና ይቅር በላቸው ፣ አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ ፣ ነፍሴን ተቀበል ... አነዚህ በሙሉ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የፀለየው ፀሎት ነው ።

አብዝቶ መፀለይ ከኢየሱስ ህይወት ያየነው እንቁ ነው !!



@cgfsd
@ownkin

👍 7
❤ 3

( #ኢየሱስ እውነተኛ የሰው ልጅ )



ወደ ከተማዋ መግቢያ በር ሲደርስም፣ እነሆ፤ ሰዎች የአንድ ሰው አስከሬን ተሸክመው ከከተማዋ ወጡ፤ ሟቹም ለእናቱ አንድ ልጅ ብቻ ነበር፤ እናቱም መበለት ነበረች፤ ብዙ የከተማውም ሕዝብ ከእርሷ ጋር ነበረ።  ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና፣ “አይዞሽ፤ አታልቅሺ” አላት።
ሉቃስ 7:12-13


ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሲቃረብ ከተማዋን አይቶ አለቀሰላት፤  እንዲህም አለ፤ “ሰላምሽ የሚሆነውን ምነው አንቺ ዛሬ በተረዳሽ ኖሮ! አሁን ግን ከዐይንሽ ተሰውሮአል፤ ጠላቶችሽ ዙሪያሽን ቅጥር ሠርተው፣ ከየአቅጣጫውም ከበው አንቺን የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣልና፤”
ሉቃስ 19:41-43

ኢየሱስም እርሷ ስታለቅስ፣ ተከትለዋትም የመጡት አይሁድም ሲያለቅሱ ባየ ጊዜ መንፈሱ በኀዘን ታውኮ፣  “የት ነው ያኖራችሁት?” ሲል ጠየቀ።
እነርሱም፣ “ጌታ ሆይ፤ መጥተህ እይ” አሉት።
ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።
አይሁድም፣ “እንዴት ይወደው እንደ ነበር አያችሁ” አሉ።
ዮሐንስ 11:33-36

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አድርጎ እንዲህ አለ፤ “የሰማይና የምድር ጌታ፤ አባት ሆይ፤ ይህን ሁሉ ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤ አዎን፣ አባት ሆይ፤ ይህ የአንተ በጎ ፈቃድ ሆኖአልና።”
ሉቃስ 10:21


#ኢየሱስ እውነትም የሰው ልጅ በመሆኑ ለሰዎች ሁሉ እውነተኛ ወገን ሁኗል ። በምድር በነበረበት ጊዜ የሰዎችን ደስታ እና ሀዘን ይጋራል ። ከልቡ ደስ ይለዋል ፣ ከልቡም ያዝናል ።  ራሱን ከህዝቡ መካከል አርቆ አይመለከትም፤ ራሱን የሰው ልጅ እያለም ይጣራ ነበር ። አብሮአቸው ይራባል ፣ አብሮአቸው ይበላል ፣ አብሮአቸው ሰርግ ይታደማል ፤ ትልቅ ማንነቱ ከእነርሱ ጋር እንዳይሆን አልከለለውም ፣  አምላክነቱ አብሮ ችግራቸውን እንዳይከፈል አልገደበውም ። ኢየሱስ የሰው ልጅ መስሎ አልነበረም በምድር ቆይታው ያለፈው እውነተኛ የሰው ልጅ ሁኖ ነው ያለፈው ።

@cgfsd
@ownkin

❤ 11
🔥 2
🥰 1

ብቻውን በውኃ ጉድጓድ ዳር ተቀምጦ የጠበቃት ኢየሱስ ጊዜን እና አደራረግን ያውቅበታል፡፡ ኢየሱስ ምንም ልንሰጠው እንደማንችልና ለእርሱ የሚመጥን ነገር እንደሌለን እያወቀ ሲቀርበን ግን በፍቅር ነው፡፡ ከትህትናው እና ከፍቅሩ ጥግ የተነሳ ሴቲቱን ሲያወራት ንግግሩን የጀመረው ጠቃሚ እንደሆነች እንዲሰማት አድርጎ ነው፡፡በቦታው እሷ መላሽ እርሱ ጠያቂ በሚመስል መልኩ ነበር ያናገራት፡፡ ተራ እንደሆነች እንዲሰማት አልፈለገም፣ ገመናዋን እያወቀ ግን በዛ መጀመር አልፈለገም፡፡ በጣም ፍቅር ስለሆነ ካላት ነገር ነው ኢየሱስ ንግግሩን የጀመረው፡፡ እንዲህ በፍቅር የቀረበን አምላክ ማን መሆኑ የእውነት ሲገባን ዝም ብለን መቀመጥ ስለማንችል ያለንን ሁሉ ትተን ለአለም ልናወራው እንሮጣለን፡፡ ከሰው ለመሸሽ በጠራራ ፀሀይ የምትወጣውን ሴት ሰው ሁሉ ወደተሰበሰበበት ቦታ ያስሮጣት የገባት የክርስቶስ ማንነት ነው፡፡ የክርስቶስን ማንነት በደንብ ስንረዳው የራሳችን ጉዳዮች ተራ ይሆኑብናል፣ የምንፈራቸው ነገሮች ሁሉ ይቀሉብናል፣ ዝም ብለን ለመቆየት ፍቅሩ ከአቅማችን በላይ ስለሆነ በየደረስንበት እናወራዋለን፡፡ በየእለቱ ይህንን ፍቅር የሆነውን ክርስቶስን የበለጠ እያወቅን መኖር ይሁንልን! ኢየሱስ ራሱ በፈለገው እና በሚገባን መንገድ ለሱ ብቻ የሚያስኖረውን፣ እንኳን ዝም ልንል እያወራነውም የማያስችለንን ፍቅሩን  ይግለጥልን!


ሉሊም
@cgfsd

🥰 11
❤ 8
🤔 1

ሰሞኑን ኢንቦክስ የተላከ ጥያቄ እንዲህ ይላል :

" ህይወታችሁን የቀየሩ ወይም ያሳደጉ 3 መፀሃፍ ቅዱሳዊ መረዳቶች አካፍሉን ?"

የበክርስቶስ ቻናል ቤተሰቦች ይሔን ጥያቄ (comment) ላይ እንመልስ ብዙዎቻችን የሚያንፅ ነገር ስለምናገኝበት

@cgfsd
@ownkin

👍 4

አቤት ግን ኢየሱስ እንዴት ያለ የማንነት ውበት ይሁን ያለው ? በእጁ ላይ ላለ ሰው እጁን ተወጋ

@cgfsd
@ownkin

❤ 21

(ኢየሱስ የመገረም ጥያቄ)



ደቀመዛሙርቱ ጌታ ኢየሱስን በታንኳ በተደጋጋሚ አብረውት ተጉዘዋል ከዛም ባለፈ አብዛኞቹ አሳ በማጥመድ ኑሯቸውን ሲደግፉ የነበሩ እንደመሆናቸው መጠን በባህር ጉዳይ ብዙም አዲሳቸው አይደለም ጥርሳቸውን የነቀሉት መረብ በማጠብ እና አሳ በማጥመድ ነው ። በምን ሰአት ማዕበሉ እንደሚነሳ በምን ጊዜ ከባድ እንደሚሆን ወጀቡን ከራሳቸው በላይ ያጠኑ ናቸው ። የእጃቸው መዳፍ ያክል በሚያውቁት ውሃ ላይ ግን ለየት ያለ ከእነርሱ አቅም የበለጠ ጉዳይ ገጠማቸው ታንኳይቱን ውስጥ ድረስ የሚዘልቅ ሀይለኛ መናወጥ መጣ ። ያኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ በታችኛው ክፍል ተኝቷል ። ከተኛበት እንዲነሳ አደረጉ አብረን እንናወጥ የሚል የግብዣ ጥሪ ቀረበለት ። ጌታ ኢየሱስ ማዕበል ወጀቡን ገሰፀው !! ከዛም ታላቅ ፀጥታ ሆነ ከቀድሞ መናወጥ በላይ የፀጥታው ዝምታ የበለጠ ልብን አሸበረ ።  ጎን ለጎን መገረምን ፣ ጎን ለጎን በጥያቄ ደቀመዛሙርቱ መወያየት ያዙ ፣ መጠያየቅ ፣ መነጋገር መታየት ጀመሩ ። ይሔ ወጀብ እና ነፍስ የሚታዘዙለት ይሔ ማን ነው ?? ይሔ ማን ነው ?? ይሔ ማን ነው ? የተከተሉት መምህር በትምህርቱ ተመስጠው ያውቃሉ ፣ ከአባቱ ሲመሰከርለትም የሰሙም አልጠፉም ፣ ፈውስ ሲያዥጎደጉድ ያውቃሉ ፣ የሞተን እንደ ተኛም ሰው ሲቀሰቅስ አይተዋል ፣ ክርስቶስ ነው ብለው ተከትለውታል አሁን ግን ከአይምሮ በላይ ሆነባቸው ይሔ ማን ነው ነፋስን የሚያዝ ዝም በል ሲል ፀጥ የሚልለት ወጀብ የሚያዳምጠው  እልፍ ወታደሮች በመንቀጥቀጥ ለንጉስ ቃል ሽርጉድ እንደሚሉ ሁሉ ፍጥረት በፊቱ ለመታዘዝ የሚያጎነብሱለት ይሔ ማን ነው ?? ።

የክርስቶስ ተከታዮች ደቀመዛሙርት እርስ በእርሳቸው የመገረም ጥያቄ ይጠያየቃሉ ። ህይወታቸውን እኮ ሰጥተውታል ፍለጋውን እየተከተሉ ነው ግን አሁንም ድረስ እየተደነቁ ይከታተሉታል ኢየሱስ ምን አይነት ልዩ ነው እያሉ ይጠየቃሉ!!

በኢየሱስ ማንነት መገረም ማንነታችን ነው ። እውነተኛ አምልኮ በኢየሱስ ማንነት ተገርመን የምንኖረው ኑሮ ነው ። የመገረም ጥያቄ  የሚጠየቀው ወደላይም እና ወደጎን ነው ።ወደ ላይ ወደ እግዚአብሔር ሲሆን በመገረም እንወቅ በማለት እንጠይቀዋለን ።ወደ ጎን ደግሞ እኛ በእርሱ ያመንን ክርስቲያኖች እርስ በእርሳችን በመካከላችን ምን አይነት ጌታ ነው በመባባል እንጠያየቃለን ።ኢየሱስ የመገረም ጥያቄ ነው ።

@cgfsd
@ownkin

❤ 11

ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት የ3 አመት ግማሽ አመት ቆይታው ውስጥ ራሱን ለመስቀል ያዘጋጅ ነበር ። በእያንዳንዱ የአገልግሎት ቆይታው ውስጥ ወደ መስቀል የሚያደርገው ጉዞ ይጠቁመናል ። ጉድ እኮ ነው በሚያሰኘው ተአምራቱ ውስጥ እሱ ወደ መስቀል ለሚያደርገውን ጉዞ ጊዜውን ይጠብቃል ፤ 2 አሳን እና 5 እንጀራን አትረፍርፎ ሰዎች በመደደመም እጃቸውን በአፋቸው ቢጭኑ እሱ ግን ከበዛው አሳ እና እንጀራ ይልክ መስቀል ላይ የሚቆረሰው ስጋ እና ደም እንደሚበረክት ይናገራል ። እሰይ ትምህርትስ እንዲህ ነው በሚያስብለው ገራሚ ትምህርቱ  መካከል መከራን ልቀበል ልሰቀል ይገባኛል  እያለ ለመስቀል ዝግጁ እንደሆነ ደጋግሞ ይሰብካል ። በስንዴ ምሳሌ እቅዱን ያስረዳል  ፤ አንዱ ስንዴ ወድቆ መሬት ውስጥ በመበስበስ በመሞት ሲያፈራ አንድ የነበረው ብዙ ሆኖ ይበቅል እያለ ለሞት የተሰናዳ የተዘጋጀ መሆኑን ከልቡ ለሚሰማው በሙሉ ያስተጋባል ። ኢየሱስ ለመስቀል ሞት የተዘጋጀበት መዘጋጀት በእጅጉ ድንቅ ነው ። ምን ያህል ርቀት ለመሞት እንደሄደ መመልከት እንችላለን ። ሲ ኤስ ሊዊስ እንዲህ ይላሉ " ለመሞት ሲፈልግ እንኳን እሱ መሞት ስለማይችል የእኛን ሞት ተበደረ " ። የማይሞተው ኢየሱስ ለመሞት የሄደው ጉዞ በራሱ የወንጌላችን ውበት ነው ። ሞትን እንኳን የተጋራን እስከ ሞት በደረሰ ወዳጅነት የተወዳጀን የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስሙ ይባረክ ።

@cgfsd
@ownkin

❤ 11
🔥 2

መታረዝ ብቻ ሳይሆን የሚታረዙትን መታደግም መስቀሉን መሸከም ነው።

Bereket kebede

@cgsfd
@ownkin

👍 12
❤ 4

Найдено 546 постов