Каталог каналов Новое Каналы в закладках Мои каналы Поиск постов Рекламные посты
Инструменты
Мониторинг Новое Детальная статистика Анализ аудитории Telegraph-статьи Бот аналитики
Полезная информация
Инструкция Telemetr Документация к API Чат Telemetr
Полезные сервисы
Защита от накрутки Создать своего бота Продать/Купить канал Монетизация

Не попадитесь на накрученные каналы! Узнайте, не накручивает ли канал просмотры или подписчиков Проверить канал на накрутку
Прикрепить Телеграм-аккаунт Прикрепить Телеграм-аккаунт

Телеграм канал «በክርስቶስ ( in christ)»

በክርስቶስ ( in christ)
736
340
3
0
8.1K
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Подписчики
Всего
1 289
Сегодня
0
Просмотров на пост
Всего
368
ER
Общий
16.83%
Суточный
12.8%
Динамика публикаций
Telemetr - сервис глубокой аналитики
телеграм-каналов
Получите подробную информацию о каждом канале
Отберите самые эффективные каналы для
рекламных размещений, по приросту подписчиков,
ER, количеству просмотров на пост и другим метрикам
Анализируйте рекламные посты
и креативы
Узнайте какие посты лучше сработали,
а какие хуже, даже если их давно удалили
Оценивайте эффективность тематики и контента
Узнайте, какую тематику лучше не рекламировать
на канале, а какая зайдет на ура
Попробовать бесплатно
Показано 7 из 736 постов
Смотреть все посты
Пост от 01.11.2025 06:38
145
0
1
ቲኪቆስ ቲኪቆስ የስሙ ትርጓሜ "ዕድል" ወይም "እድለኛ" ማለት ነው:: ቲኪቆስ "ከእስያ" አካባቢ [ሃዋሪያው ጳውሎስ እንደተናገረው ሐዋ. 20:4] ከኤፌሶን ወይም ባቅራቢያው ካሉት ከተሞች እንደመጣ ይታመናል:: በእርግጥ ቲኪቆስ ከጳውሎስ ጋር በሦስተኛው የጳውሎስ የወንጌል ሥርጭት ጉዞ [ጳውሎስ ከግሪክ ወደ ኢየሩሳሌም በሔደ ጊዜ] አብሮ እንደነበር ራሱ ሃዋርያው ተናግሯል (ሐዋ. 20:4):: ቲኪቆስ ግንባር ቀደም በመሆን በወንጌል ሥራ ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ስማቸው እንደተጠቀሱት እንደነ ጴጥሮስ፣ ጳውሎስ፣ ዮሐንስ፣ ወዘተ አይሁን እንጂ፤ ከግንባር ቀደሞቹ ጀርባ ከነበሩት ድንቅ የወንጌል አገልጋዮች ተርታ የሚሰለፍ ወንድም ነው:: ስለ ቲኪቆስ የጳውሎስ ምስክርነቶች በጥቂቱ:- 1. ቲኪቆስ "የተወደደው ወንድም" ነው (ኤፌ.6:21፣ ቆላ. 4:7) 2. ቲኪቆስ "የታመነ አገልጋይ" ነው (ቆላ.4:7) 3. ቲኪቆስ "በጌታ ኢየሱስ ሥራ ታማኝ አገልጋይ" ነው (ኤፌ.6:21) 4. ጳውሎስ "በጌታም አብሮኝ ባሪያ የሆነ" በማለት ስለ ቲኪቆስ መስክሯል (ቆላ.4:7) 5. ጳውሎስ በቆላስይስ 4:11 ላይ "በእግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩት እነዚህ ብቻ ናቸው፥ እኔንም አጽናንተውኛል" ብሎ በስም ከጠቀሳቸው ወንድሞች መካከል አንዱ ቲኪቆስ ነው 6.  ጳውሎስ ከአናሲሞስ ጋር የቆላስይስን ደብዳቤ አስይዞ የላከው ሰው ቲኪቆስ ነው (ቆላ. 4:6-7) 7. ቲኪቆስ ምንአልባትም ጳውሎስ ቲቶን "ለተወሰነ ጊዜ" እንዲተካው ወደ ቀርጤስ ልኮት ሳይሆን አይቀርም (ቲቶ. 3:12) እንዲሁም ወደ ኤፌሶን ጢሞቴዎስን ለተወሰነ ጊዜ እንዲተካ ስለ መላኩ ፍንጮች አሉ (2ጢሞ. 4:12) 8. ቲኪቆስ የጳውሎስ የቅርብ ሰው፣ የወንጌል አገልጋይ፣ በወንድሞች መካከል በጤናማ የወንጌል አገልግሎት የተጋ በህይወት ምስክርነቱም የታወቀ ሰው ነበር:: ከላይ በጥቂቱ ከዘርዘርኳቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንደምንረዳው፣ ቲኪቆስ:- - በምንም ማዕርግ ወይም የአገልግሎት መለያ አይታወቅ እንጂ የአገልግሎትና የሕይወት ምስክርነቱ ግን በቅዱሳን ዘንድ የታወቀ ሰው ነበር:: - ለጳውሎስ የወንጌል አጋር ብቻ ሳይሆን የኑሮም አጋር ነበር:: "ኑሮዬን ያስታውቃቹሃል" ያለውን ልብ በሉ (ቆላ. 4:7) - በወንጌል ምክንያት ታስሮ በብቸኝነት ለነበረው ጳውሎስ መጽናናት የሆነ ሰው ነው - እውነተኛው አስተምህሮ (orthodoxy) ከህይወት ምስክርነቱ (Orthopraxy) የማይጣላበት ሰው ነበር:: - ታማኝ ነው፣ የተወደደ ነው፣ አገልጋይ ነው፣ መልዕክተኛ ነው፣ ወዘተ ቲኪቆስ በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ሆነ በአሁኗ ቤተክርስቲያን ከ"መጋረጃ ጀርባ" ወይም "behind the scene"ወይም "ያልተዘመረላቸው ጀግኖች" ወይም "unsung heros" ለሆኑ ብዙ አገልጋዮች እንደ ምሳሌ የሚቀርብ አገልጋይ ነው:: ለአንድ የወንጌል አገልጋይ ስም ሳይሆን የህይወት ምስክርነት፣ ማዕረግ (title) ሳይሆን ለወንጌል ታማኝነት መሠረታዊ ጉዳይ እንደሆነ ያስተማረም ሰው ነው ቲኪቆስ:: ✍️ Eyob B kassa @cgfsd
🔥 6
2
Пост от 29.10.2025 12:01
331
0
1
( የእግዚአብሔር ውበት) ፍጥረት በዝምታ የእግዚአብሔርን እፁብ ድንቅነት ይመሰክራሉ ። ታሪክም ከእግዚአብሔር በቀር ሃያል እንደሌለ ያሳብቃል  ። በቅዱሱ መፀሃፍ የተገለጠው የእግዚአብሔር የማንነትና የስራው ውበት ይለያል ! አስደናቂው ባህሪው ውስጥ እንከን የለሽ ፍፁም ትክክል ስራው ይታያል ። በተቀያየሩ ሰዎች ውስጥ ያልተለወጠ እቅዱ ፣ ደጋግሞ ሰውን መቅረብ ፣ በሰው መካከል ለመኖር አጎንብሶ መምጣቱ ፣ በሰው ቋንቋ እኔ ማለት ብሎ በሀ ሁ ራሱን መግለፁ ግሩም ነው ። ከመፀሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ድረስ የሚታየው ይሔ አስደናቂው አምላክ ያለው የማንነት ውበት ነው ። መፀሃፍ ቅዱሱን በትክክል ያነሳ በእግዚአብሔር ማንነት መገረም ውስጥ ደጋግሞ ይወድቃል ! @cgfsd
16
🔥 6
Пост от 24.10.2025 12:49
445
0
6
....ስለዚህ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ አዝኖ የፍጥረቱን መከራ የራሱ አድርጎ ወሰደ ። ጎልጎታ ከዚህ የእግዚአብሔር ሐዘኔታ ይመነጫል ። እናም በጎልጎታ ኮረብታ ላይ መስቀል ከመተከሉ በፊት በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ መስቀል ተተክሎ ነበር ። መስቀሉ ከጎልጎታ ኮረብታ ቢነቀልም ፣ በእግዚአብሔር ልብ ላይ ያለው መስቀል ግን እስካሁንም አለ ።            የተሰቀለው  (ጳውሎስ ፈቃዱ)
18
🔥 4
🥰 3
😢 2
Пост от 24.10.2025 11:02
407
0
4
እጅግ ውብና ህይወት ያለው ታሪክ 👉 የክርስቶስ ዘላለማዊነት ፣ መወለድ ፣ መሞት ፣ መነሳት ፣ ማረግ ፣ በአብ ቀኝ መቀመጥ ፣ ተመልሶ ዳግም መምጣት!
🔥 13
10
👍 1
Пост от 22.10.2025 23:12
511
0
4
መዝሙር 🎶 እምነት! በይሳኮር ጌታቸው @cgfsd
Звукозапись
14
Пост от 21.10.2025 10:28
430
0
3
(አይ ወንጌል)                  ክፍል 4- ስንቅ ማቀበል ሽበት የወረራቸው ግርማ ሞገስ የተከናነቡ መጋቢ በአካባቢ አጠራራር አባት ልናገኛቸው ወደ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ስንገባ በአዳራሽ ውስጥ ተንበርክከው ብቻቸውን እየፀለዩ ነው ። የጳጉሜ ፀሎት መርሃ ግብር በመሆኑ ለመፀለይ እንደመጡ ገምተናል ። ነገር ግን ማንም ሳይኖር በጠዋት ማልደው በጊዜ ብቻቸውን መፀለያቸው አስደነቀን በዛላይ እድሜያቸው ገፍቷ ። አቤት ትጋት! ግርማ ሞገስ የጠገቡት መጋቢ  ረጅም ተክለ ቁመና ከተላበሰው ገፅታቸው ላይ እንደ ጥጥ እርሻ ሸበት የወረረው ፀጉራቸው ልዩ ገፅታ ሰጥቷቸዋል ።  በተጨማሪ አንደበታቸው ራሱ ይጣፍጣል ። ወንጌል ከሰሙ በኋላ  ለወንጌል ስራ ከተለዩ ወደ አርባ አመት ይጠጋል ። እንደዚህ ታሪካቸውን ያጋሩን ጀመሩ " አዲስ አማኝ ሁኜ ከእኔ በፊት ከቀደሙ ክርስቲያን ስር ስር ያልኩ የወንጌልን ሀ ሁ መማር ያዝኩኝ ። የስደት ወቅት ስለነበረ አማኞች በድብቅ አምልኮአችን እናደርጋለን ። በግለሰብ ቤት አዘወትረን የፀሎትና ቃለ እግዚአብሔር እንማር ነበር ። አንድ ትልቅ አባት ሊያስተምሩን  ከሩቅ ስፍራ መጡ ፤ እሳቸው ለቀናት እያስተማሩን ቆዩ ። አንድ ቀን በመንገድ ላይ ንብረታቸውን ስለጣሉ ከነበሩት መካከል በእድሜ አነስ የምለው እኔ ስለሆንኩ እኔን ይዘውኝ የጣሉትን ንብረት ፍለጋ  ወጣን ። ለፍለጋ በወጣንበት ፖሊሶችና አብዮት ጠባቂዎች መጥተው በቤት የነበሩን አማኞች ጠራርገው ወደ እስር ቤት አስገቧቸው ። እኛም ሀገር አማን ነው ብለን ስንመለስ ቤቱ ወና ነው አንድም ሰው የለም ። ታፍሰው እንደሄዱ ሰማን በዘመኑ የነበረው መከራ ስለምናቅ አዘንን ። እኔ ልጅም ስለሆንኩ እጄን ሰጣለው አብሬያቸው እታሰራለሁ ብዬ ተነሳሁ ። አብሮኝ የነበሩት አባት አይሆንም አንተ እኮ ያልታሰርከው ለወንጌል ስራ እስር ላሉት ስንቅ እንድታቀብል ቢሆንስ ፤ በጦርነት ጊዜ ሁሉም አይዋጋም ስንቅ የሚያቀብሉ በወጊያ ግንባሩ ላሉት ሀይል ደጀን ይሆናል ። እናም ተግተህ የሚያስፍልጋቸውን አሟላ በእስር እንዳሉ አበርታቸው እነሱ በዛው ወንጌል ያስቀጥሉ አለኝ ። ከዛም በእየ ወረዳው እየዞርኩ ከአማኞች ምግብ እያመጣሁ 14 ታሳሪ የነበሩን አማኞች ስንቅ ማቀበል ያዝኩ ። በኋላ ገባኝ ለካ ለዚህ ነው እኔ ያልታሰርኩ በዚህ መልኩ ወንጌል ለሚሰሩ አቅም እንድሆን ብዬ ስለሰጠኝ ሌላ ስንቅ የማቀበል አገልግሎት እድል ጌታን አመሰገንኩ ። በኋላ ሲፈቱ 14 የነበሩት ታሳሪዎች ለሌላ 14 ሰው ወንጌል መስክረው  28 አማኝ ሁነው ተፈቱ ። "  ባለሞገሳሙ መጋቢ ታሪካቸው ቀንጭብው እንዲህ አጋሩን ። በወንጌል አገልግሎት ውስጥ ስንቅ ማቀበል ትልቅ የአገልግሎት እድል ነው ። መጋቢው በእስር ላሉት የወንጌል አገልግሎት ስንቅ ለማቀበል የተሰጣቸው ትልቅ የእግዚአብሔር ሀላፊነት እንደሆነ በማመን ያደረጉት እርምጃ ለሌሎች መዳን ምክኒያት ሁኗል ።  ስንቅ ማቀበል የግድ ስንቅ ብቻ መሆን የለበትም የምንችለውን ትንሽ ነገር ለእግዚአብሔር መንግስት ስራ ጠብ ማረግ ስንቅ ማቀበል ነው ። የምናቃቸው ሚሽነሪዎች ስንቅ አቀብለናቸው ይሁን ? በፀሎት መደገፍ አንድ መንገድ ነው ። ወንጌል ሰባኪ እንዳለ ሁሉ ለወንጌል አገልግሎት መፍጠን ስንቅ ማቀበልም ትልቅ አገልግሎት ነው ። የፊልጵስዩስ ቤተክርስቲያን ለእስረኛው ጳውሎስ ወንጌል ስራው የበለጠ እንዲፈጥን በአፍሮዲጡ በኩል ስንቅ ለማቀበል የተወሰነ ድጋፍ አደረጉ በጳውሎስ የወንጌል አገልግሎት ባቀበሉት ስንቅ ተሳታፊ ሆኑ (ፊል2)። የስንቅ አቀባይነት አገልግሎት ቸል አንበለው ። ስንቅ አቀባይ የሚፈልጉ ብዙ እውነተኛ የወንጌል አገልጋዮች በገጠር ከተማ አሉ ። @cgfsd
11
🔥 4
🥰 2
Пост от 08.10.2025 07:46
281
0
2
ከማኑሄ ለምን ጥቂት አንማርም ? ----------- ማኑሄ፣የሳምሶን አባት ነው።እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ፊት በማመጻቸው ምክንያት በፍልስጥኤማውያን እጅ ለ40 አመታት የተገዙበት ወቅት ነው ።ምንም እንኳን "ይህን ብቻ ይቅር በለን "ያሉ እስራኤላውያን መልሰው ጣኦታትን በማምለክ እግዚአብሔር ቢቆጠባቸውም እንዲጎሳቆሉ ግን አይወድም ነበር ።ይህን ሕዝብ እንድታደግ ከመካን ሴት ለእግዚአብሔር ልጅ ነበረው ። የእግዚአብሔር መልአክ ለሚስቱ ነበር የተገለጠው።ማኑሄ በቦታ አልነበረም ።ሚስቱ መጥታ ስትነግረው ግን ለማመን ምንም ያገደው ነገር አልነበረም ።"ምናልባት ቅዠት ይሁን" አላለም ፤ "እርግጠኛ ነሽ አጣርተሻል " ብሎም አላስጨነቃትም። ምናልባት ባልና ሚስት ናቸውና ተመሳሳይ የጸሎት ርዕሰ ሳይኖራቸው አልቀረምና ወዲያውኑ ነበር  የሚስቱን ብስራት የተቀበለው ።ሳስበው ጥሩ መተማመንም ነበራቸው ።ባልና ሚስት ማለትም ይኼ ነው ! ከዚህ ሁሉ የገረመኝ ማኑሄን  ያጨናነቀው ነገሩ እውነት ይሁን ወይስ የሚስቴ ቅዠት ነው የሚለው ሳይሆን የሚወለደው ልጅ የሚያድግበት መስመር ነበር ።አቤት !እምነት ያለው ሰው ! እግዚአብሔር የተናገረውን እንደሆነ ቆጠረው ።“ከዚያም ማኑሄ፣ “ጌታ ሆይ፤ የሚወለደውን ልጅ እንዴት አድርገን ማሳደግ አንዳለብን እንዲያስተምረን ያ ወደ እኛ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እንደ ገና እንዲመጣ ታደርግ ዘንድ እለምንሃለሁ”። ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።” መሳፍንት 13:8 አመት። ደጉ ጌታም ጸሎቱን መለሰለት ።ሚስቱ በሁለተኛው ዙር እሱን ጠርታ ከእግዚአብሔር መልአኩ ጋር ብታገናኘውም፣ አሁንም የእርሱ ጥያቄ "እውነትም ለሚስቴ ተናግረሃታል ?"የሚል አልነበረም ፤ይልቁንስ “ማኑሄም፣ “ያልኸው በሚፈጸምበት ጊዜ የልጁ ሕይወት የሚመራው እንዴት ነው? እኛስ ምን ማድረግ አለብን?” ሲል ጠየቀው” የሚል ነበር ።   — መሳፍንት 13፥12 አመት። ማኑሄ እግዚአብሔር የተናገረውን ሊቀበል አንድ እርምጃ ሄዶ የሚጠብቅ የእምነት ሰው ነበር ። እርሱ ለሚስቱ የነበረው አመለካከት ጥሩ ባል ነበር ማለት ያስችለናል (ባሎች ከማኑሄ ተማሩ)። ማኑሄ እግዚአብሔር የተናገረውን ገና ከመቀበሉ በፊትም ለእግዚአብሔር መስዋዕት ማቅረብ የቻለ ፤አምላኩን በአይኑ በማያቱ ወዮልኝ ያለው የአምላኩን ከብር ጠንቅቆ ያወቀ ሰው ነበር ። እግዚአብሔር ሲናገረን አንድ እርምጃ ሄደን የመቀበል እምነት ይጨመርልን።እሱ ከተናገረ ሆነ ነው በቃ! ✍ ብሩክ ተመስገን @cgfsd
23
🥰 2
🔥 1
Смотреть все посты