Телеграм канал 'በክርስቶስ ( in christ)'

በክርስቶስ ( in christ)


690 подписчиков
97 просмотров на пост

Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin

Детальная рекламная статистика будет доступна после прохождения простой процедуры регистрации


Что это дает?
  • Детальная аналитика 5'661'587 каналов
  • Доступ к 1'533'798'153 рекламных постов
  • Поиск по 5'927'925'286 постам
  • Отдача с каждой купленной рекламы
  • Графики динамики изменения показателей канала
  • Где и как размещался канал
  • Детальная статистика по подпискам и отпискам
Telemetr.me

Telemetr.me Подписаться

Аналитика телеграм-каналов - обновления инструмента, новости рынка.

Найдено 571 пост

ይሔን መዝሙር ተጋበዙልኝ !!


የእግዚአብሔር ሀሳብ በዚህ ልክ ይዘመራል ወይ ?

እግዚአብሔር እንዴት ይመሰገናል ? በምን ይመሰገናል ? የሚለውን ጥያቄ ይመልሳል ። እግዚአብሔርማ በልጁ በሰራው ስራ ምክኒያት በኢየሱስ በኩል ይመሰገናል ። እግዚአብሔርን ማመስገን የፈለገ በኢየሱስ ስም በኩል ያመስግን ። እንዴት ያለን እድለኞች ነን ... እግዚአብሔርን በልጁ ኢየሱስ እናመሰግነዋለን ። ማመስገኛ አለን ፣ ምስጋና የምንልክበት አለን ። እግዚአብሔር የሚያስደስተው ምስጋና በኢየሱስ ስም በኩል የሚደርሰው ምስጋና ነው።

እግዚአብሔር ሆይ ምህረትን ፣ፍቅርን ፣ ዘላለማዊ ህይወትን ፣ ፅድቅን በላክልን በኢየሱስ ስም በኩል አንተም ስላረከው ነገር ሁሉ በኢየሱስ ስም ተመስገን ።

@cgfsd

❤ 5
🥰 1

(የጌተሰማኒው አልቃሽ )

  #በታላቅ ጩኸት እና እንባ የተፀለየ ፀሎት😭

ኢየሱስ በዚህ ምድር በኖረበት ዘመን ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ልመናን ከታላቅ ጩኸትና ከእንባ ጋር አቀረበ፤ ፍጹም ትሑት ሆኖ በመታዘዙም ጸሎቱ ተሰማለት።
ዕብራውያን 5:7


#ከመጨነቅ የተነሳ በብርቱ የተፀለየ ፀሎት😭


እጅግ ተጨንቆም በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም እንደ ደም ነጠብጣብ ወደ ምድር ይፈስ ነበር።
ሉቃስ 22:44



#በግንባሩ በመደፋት የተፀለየ ፀሎት 😭

ጥቂት ዕልፍ ብሎ በግንባሩ በመደፋት፣ “አባቴ ሆይ፤ ቢቻል ይህ ጽዋ ከእኔ ይለፍ፤ ነገር ግን እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን አንተ እንደምትፈልገው ይሁን” ብሎ ጸለየ።
ማቴዎስ 26:37-39


#ምድር ላይ በመውደቅ የተፀለየ ፀሎት 😭

ጥቂት ዕልፍ ብሎም በምድር ላይ በመውደቅ ቢቻል ሰዓቱ ከእርሱ እንዲያልፍ ጸለየና፣
ማርቆስ 14:35


ኢየሱስ😭 እንዴት ቢፀልይ ይሁን ግን ?


@cgfsd
@ownkin

❤ 13

ቅዱስ ማቴዎስ እንደሚነግረኝ ጌታዬ ኢየሱስ ከመወለዱ ጀምሮ በኃያላን ሊቀላ የሚፈለግ ስደተኛ ተፈናቃይ ሕጻን ነበር። ከተፈናቀለበት ሲመለስም ወደቤቱ ሊመለስ ስላልቻለ በናዝሬት አደገ። በውሃ ተጠምቆ ሲወጣ ከሰማይ የተወደደ ልጅ መሆኑ ቢነገርለትም በገዛ ቀየው የተገፋ ማስጠንቀቂያው ትምህርቱ ልምምዱ ሁሉ ብዙ ንትርክ የሚያስነሳበት ዓይነት ነበር። ስልጣን አልነበረውም የሚያደርገውን ሁሉ በምን ስልጣን እንደሚያደርግ ማብራራት ይጠበቅበት ነበር። የሚበላውን ሌሎች የሚሰጡት ድኻ ነበር።
እርሱ ግን ለማስረዳት በሚከብድ ኃይል የተሞላ ነበር። በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ወደምድረበዳ ሄዶ ለአርባ ቀናት ተርቦና ተጠምቶ፣ በሰይጣን ተፈትኖ ይመጣል። ሕሙማንን ሲነካ ይፈወሳሉ አጋንንት በፊቱ ይርዳሉ። እውነትም ኃያል በማለት የመጥምቁ ዮሐንስን ምስክርነት ለማጽናት እገደዳለሁ። ከማቴዎስ ገጾች ላይ ብቅ የሚለው በስደት የሚኖረው ተፈናቃዩና ጎዳና አዳሪው ኢየሱስ በአንዳች ኃይል የተሞላ የተስፋ ገንቦ ሆኖነው።
ብጹዕ ሆኖ በመንፈሱ ድኻ የመንግሥተ ሰማያት የእርሱ የሆነ የሚገባ ሌሎችን የሚያስገባ ድኻ የሚያዝን የሚጽናናና ሌሎችን አልቃሾች የሚያጽናና። የዋሕ በመስቀሉ ሞት ምድርን የሚወርስ ቀሊል ቀንበሩን ሌሎች ላይ አድርጎ ራሳቸውን ወደመካድ የሚመራ ልዝብ ልስልስ መሪ ዓለምን የሚያንበረክክ ጽኑ ፍቅር። ጽድቅን የሚራብ የሚጠማ የሞቱን ጽዋ ጨልጦ የራሱን ብቻ ሳይሆን የሌሎችን የጽድቅ ረሃብ የሚያረካ። ምህረትን የሚያደርግ ለጠላቶቹ የሚሞት በእግዚአብሔር አብ የትንሳዔን ምህረት የሚያገኝ፣ የትንሳዔን ምህረት የሚያስገኝ።ሰላምን የሚያወርድ ጨቋኞቹ እየሰቀሉት የሚመሰክሩለት እውነትም ይኽ ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ነበር ማቴ27፥54 ። ስለጽድቅ ብሎ የተሰደደ ባለመንግሥት። እኔ ደካማዋ ላይ በረከትህ ይውረድብኝ ጌታዬ!

✍ ሳራ ከድር

❤ 12
Изображение

(አኗሪ )

ክርስቶስ በልባችን ማኖር የእኛ ስራ አይደለም በልባችን የሚያኖር አካል አለ እርሱ መንፈስ ቅዱስ ይባላል ። መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስን በልባችን ላይ ለማኖር ብዙ ኢንቨስትመንቶችን ያረጋል ። እኛን በህልውናው ያውደናል ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እንድንለማመድ የቀመስነውን ፍቅር መልሶ መላልሶ ያስታውሰናል ፣ በልባችን ሊኖር የተገባውን ክርስቶስ ማን እንደሆነ ይነግረናል ፣ እኛ የተረጨንበትን ክቡር ደም ያሳስበናል ።

ክርስቶስን በልባችን ማኖር የመንፈስ ቅዱስ ድርሻ መሆን ካወቅንበት አንዱ ምክኒያት መካከል ክርስቶስን በልብ ማኖር የሚቻለው በውስጥ ሰውነት በመንፈሱ በኩል በመጠንከር ስለሆነ ነው ።
 
በውስጥ ሰውነት መጠንከር በውስጠኛው ማንነታችን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሚኖር ጣፋጭ ህብረት በሀሳብ ፣ በዕውቀት ፣ በስሜት ፣ በፈቃዳችን መንፈስ ቅዱስ ላይ ጥገኛ መሆን ነው ። በመንፈስ ቅዱስ ውስጠኛው ሰውነታችን ሲበረታ ልባችን ክርስቶስ ለማኖር ዝግጁ ይሆናል ። ሀሳባችን ፣ ስሜታችን ፣ ፈቃዳችን ክርስቶስ ለማኖር ይጓጓሉ ።በመንፈሱ በውስጥ ሰውነት መጠንከር ክርስቶስ በልባችን እንዲኖር ልባችንን ብቁ ያደርገዋል ።

@cgfsd
@ownkin

❤ 15
👍 3

(ቤተኝነት ለቤተኛው )


ክርስቶስ በልባችሁ እንዲኖር ብሎ ሲፀልይ ሐዋሪያው ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ወደ እናንተ ማንነት የገባው ክርስቶስ እናንተ ለቤትነት ይፈልጋችኋል እያለ ነው ። የክርስቶስ ቤተመቅደስ ናችሁ ማለት የክርስቶስ መኖሪያ ቤት ናችሁ ማለት ሲሆን ክርስቶስ በልባችሁ ይኑር ማለት ግን እናንተ ቤት ያደረጋችሁ ክርስቶስ ቤተኝነት ይሰማው ፣ በራሱ ቤት ነፃነት ያግኝ፣ የደም ዋጋ ያወጣበት የቤቱን ባለቤትነት ማንም አይጋራው።

ክርስቶስን በልባችን ማኖር በነፍሳን ላይ ቤተኛ እና ባለቤት ማድረግ ነው ።

@cgfsd
@ownkin

❤ 14
👍 1

(እየኖረ የሚኖር)


ክርስቶስ በመስቀል ላይ በከፈለው ድንቅ መስዋትነት የተነሳ እኛን ቤተ መቅደስ አድርጎ በእኛ ውስጥ ይኖራል ። ክርስቶስ ኗሪ ነው ። በደሙ በሰራው ፣ በደሙ ባጠበው በመስቀል ላይ ሙቶ ባቆመው መቅደስ ሊኖር አለ ፤ በመንፈሳችን ውስጥ ይኖራል ። ነገር ግን በመንፈሳችን ውስጥ እየኖረ እንዳለ ሁሉ በዕለት ተዕለት ኑሮ በልባችን ሊኖር ይፈልጋል ። ልብ ማለት ሀሳብ፣ እውቀት ፣ ፈቃድ ፣ስሜት ሁሉ ጠቅልሎ የያዘ ነው ። ክርስቶስ በልብ ይኑር ሲባል በዕውቀታችንም፣ በሀሳባችን፣ በፈቃዳችንም ፣ በስሜታችን ውስጥ በሙሉ እሱ እየኖረ በስሜታችን እሱ ሊሰማው ፣ በፈቃዳችን ላይ እሱ ሊፈቅድ፣ በዕውቀታችን ውስጥ እሱ ሊያውቅ፣ በአስተሳሰባችን ውስጥ እሱ ሊያስብ ክርስቶስ በልባችን ሊኖር በእኛ ውስጥ አለ ። ክርስቶስ እየኖር የሚኖር ነው ።

@cgfsd
@ownkin

❤ 14
🥰 7

ኢየሱስ የራሱን መንግስት ያስተዋወቀው  እሱ ራሱ በመንግስቱ ውስጥ ንጉስም ወታደርም በመሆን ነው ።


@cgfsd
@ownkin

❤ 15
👍 2

(67ተኛ መፀሀፍ)


  በመልካም ምግባሩ ፣በሰባአዊነቱ ተጠቃሽ ከሆኑት ሰዎች መካከል አንዱ ማህተመ ጋንዲ አንዱ ነው ። ጋንዲ በኖረበት ዘመን ዝናው በአለም ላይ ናኝቶ ነበር ።  ለተወሰኑ አመታት  በተሰማራበት የህግ ሙያው ተቀጥሮ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዲመጣ ሆነ ። በደቡብ አፍሪካ ቆይታው በዘሩ ምክኒያት ነጮች ያሰቃዩት ፣ያገሉት ሲያሻቸው ያወግዙት እንደነበር እራሱ ይናገራል ። እዛው ደቡብ አፍሪካ በነበረበት አመታት ከክርስቲያኖች ጋር ይገናኝ ፣ ይነጋገር አልፎ አልፎ በመፀሀፍ ቅዱስ ጥናታቸው ይሳተፋል ። በተለይ ከእሱ ጋር ቅርብ የነበረው ሰው በተደጋጋሚ የመዳን ብቸኛ መንገድ ክርስቶስ በማመን እንደሆነ ያበስረዋል ። ጋንዲም በግሉ መፀሀፍ ቅዱስ ሲያነብ፣ ሲሰበክም ከሚሰማው በጠቅላላ የክርስቶስ ህይወት እንደሚማርከው ይናገራል ። ጌታን እንደግል አዳኙ አርጎ ግን  አልተቀበለም!!!!! ጋንዲ እንዲህ  አለ " ክርስቶስን እወደዋለሁ ክርስቲያኖች ግን እንደእሱ አይደሉም "።
    ለጋንዲ ካነበበው መፀሀፍ ቅዱስ እና ከሰበኩለት ክርስቶስ የክርስቲያኖች ህይወት ርቆበታል ።
  
   መፀሀፍ ቅዱስ 66 መፀሀፍት ጠቅልሎ ይዟል  እነርሱም ፤ የብሉይ 39፣  አዲስ ኪዳን 27 ናቸው።  አንበብን ይሆናል ወይም ደግሞ ከጥግ እሰከ ጥግ ሸምደደውም ሊሆን ይችላል  ነገር ግን መፀሀፍ ቅዱሳችን 67 እንደሆነ እናውቃለን ወይ ??? ወይስ አናውቅም ??? እውነት ነው ግራ ሊገባን ይችላል በመፀሀፍ ቅዱሳችን ያሉት መፀሀፍት 66 ነው ነገር ግን አንድ ክፍት አለ 67ተኛው መፀሀፍ እርሱም የክርስቲያን ህይወት ነው ። ጋንዲ ምናልባት ስልሳ ስድስቱን አንብቦ 67ተኛውን ከአማኞች አቶት ይሆን ??? ወንጌል የምንሰራ በአለማዊያን ፊት ለምንመላለስ 67ተኛው ሁኖ ሊናገር ክርስቶስ ሊያሳይ የሚችለው ህይወታችን ነው ። 67ተኛው መፀሀፍ የክርስቲያን ህይወት ነው !!
 

  መፀሀፍ ቅዱሳችን  መነበብ እንደሚገባን መክሮናል ። ሊነበብ ይገባል !!!" 67ተኛው መፀሀፍ ያልተፃፈ ግን የሚታይ የዕለት ተዕለት ኑሮአችን ነው የበለጠ ሊነበብ ይገባል ።


✍  ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd

❤ 15
👍 1

ዓለምን ያነጋገረው የይቅርታ ልብ!

ሰሞኑን መነጋገሪያ የሆኑት በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው በአሦርያውያን ቤተ ክርስቲያን የአውስትራሊያ ጳጳስ የሆኑትና
በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በሚዘዋወሩ ክርስቶስ ተኮር ስብከታቸው የሚታወቁት አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል በአገልግሎት ላይ ሳሉ የተፈፀመባቸውን ጥ*ቃት ብዙዎቻችሁ እንደሰማችሁት ጥርጥር የለኝም፤

እጅግ በጣም የገረመኝ ነገር ግን አክራሪ ሙ'ስሊም የሆነው ወጣት በቪዲዮ ላይ ሲዘወወር እንዳያችሁት ደጋግሞ ጥ*ቃት ቢያደርስባቸው የመጀመሪያ ያደረጉት ነገር እንደምንም አቁሙኝ ብለው በአጥቂው ራስ ላይ እጃቸውን አድርገው መጸለይ መጀመራቸው ነው። እንዴት ያለ አስደናቂ የይቅርታ ልብ ነው ወዳጆቼ?

እንደ እርሳቸው እየ*ወጉት የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ያለውን የክርስቶስን ፈለግ በሕይወት መከተል የምንችልበት፤ በመወጋታችንም ቢሆን
ለሚሊዮኖች ክርስቶስ እንዲሰበክ ምክንያት የምንሆንበት ፀጋ ይብዛልን።

✍️አክሊሉ ተስፋዬ

@cgfsd

🥰 7
👍 3
🔥 1

በልባችን ውስጥ ሊኖር እኛን ቤተ መቅደስ አደርጎ ይሔው አዲስ መኖሪያ ብሎ በደሙ መረቀ ። ወደ አባቱ እንድንገባ ወደ ዙፋኑ የሚንገባበትን መንገድ ይሔው ብሎ በደሙ መርቆ መንገዱን ከፈተው ።

  ኢየሱስ ስጋው እየቆረሰ ደሙን እያፈሰሰ ይሔው አዲሱ መኖሪያ ይሔው አዲሱ መንገድ በማለት መርቆታል ።

@cgfsd
@ownkin

❤ 18
🔥 3
👍 1

(ክርስቶስ በየትኛው ልብ ውስጥ የሚኖረው ?)


#በክርስቶስ ደም በተረጨ ልብ ውስጥ

#በመንፈስ ቅዱስ በኩል የእግዚአብሔር ፍቅር በፈሰሰበት ልብ ውስጥ

#የእግዚአብሔር ታላቅ ምህረት ያረፈበት ልብ ውስጥ

#ክርስቶስ ኢየሱስ ይመጣል በሚል ግሩም ተስፋ በተሞላ ልብ ውስጥ

#በእግዚአብሔር የህልውና መአዛ በታወደ ፤ በታጠነ ልብ ውስጥ

#ኢየሱስ የሚለውን ስም ሁልጊዜ እንዲጠራ ፈቃድ በሰጠው ልብ ውስጥ

#ክርስቶስ ኢየሱስ  በራሱ ለራሱ በዋጀው ልብ ውስጥ


        ክርስቶስ ኢየሱስ የሚኖርበት ልብ ራሱ ክርስቶስ ባፈሰሰው ደም የደመቀ፣ በቅዱስ መንፈሱ የተዋበ፣ በጥልቅ ፍቅሩ ያሸበረቀ ፣ በድንቅ ስሙ ያበራ፣ በአስደናቂው ፀጋ የተጥለቀለቀ፣ በተባረከው ተስፋ ኢየሱስ በኩል የታወደ፣ ውድ በሆነው ምህረቱ የሚያብረቀርቅ ልብ ውስጥ ክርስቶስ ይኖረናል ።

     " ኢየሱስ ሌላ ምንም አላለንም ደም ባፈሰስኩበት ልብ ውስጥ ልኑር "

@cgfsd
@ownkin

❤ 16
👍 1
😢 1
Изображение

ዛሬ በዙዎች በተራሮች፣ በትልልቅ አብያተ ክርስቲያናት፣ በድንጋይ እና በፍሬም ህንፃዎች ይሰግዳሉ። ኢየሱስ ግን መዳን በእነዚህ የድንጋይ ሕንጻዎች ውስጥ እንዳልሆነ ያስተምራል በተራሮች ላይ አይደለም በተራሮች ላይ አይደለም ነገር ግን በእግዚአብሔር ነው የዳነ እና የተቀደሰ ማንኛውም ሰው የኢየሱስን ስም ሲጠራ በልቡ ውስጥ እሳት ሲነድ ይሰማዋል። በህይወታችን በእያንዳንዱ ጊዜ የኢየሱስ ክርስቶስን ደም እናክብር፣ እናም በነፍሳችን ጣፋጭ እንሆናለን።

ዊሊያም ጄ ሲሞር

@cgfsd

❤ 16

(ጌታ ኢየሱስ )



አንዳንድ ቀኖች የየራሳቸው መለያ አላቸው ። ሐሙስ የቀን ንጉስ ብለን ዘክረናል ፣ አርብ ከኋላ ላሉት 2 የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናቶች እንደ ማጣፈጫ ቅመም  ቆጥረናል ። የዛሬ አንድ አመት በፊት የአርብ ፕሮግራም (friday service) ለመካፈል ረፈድፈድ አድርጌ ነበር የወጣሁት ። ጓደኞቼን ዛሬ ብዙ ሰው አለ ቦታ እንዳይሞላብህ  ይዘንልሃል አርፍደሃል ትንሽ ከቆየህ ጥሩ ቦታ አታገኝም እያሉ ሜሴጅ በተደጋጋሚ ላኩልኝ ። እንደደረስኩ የተያዘልኝ ቦታ ወደ መጨረሻ አካባቢ ነበር ፤ ከፊት ለፊቴ መድረኩን ስመለከት በግማሽ ምሶሶ ይጋርደኛል ምቾት ባይሰጠኝም ምንም ምርጫ ስላልነበረኝ በግማሽ መድረኩን አያለሁ በሚል ተስፋ ተደላድዬ ተቀመጥኩ ።

የአምልኮ ጊዜ አለቀ ። ወደ መጨረሻ ስለተቀምጥኩ ወደ ፊት አካባቢ ጨለም ብሎ ነበር የሚታየኝ ። የዕለቱ ፕሮግራም መሪ ዛሬ ቃል የሚያስተምረን  ጋሽ አብዱ ናቸው ብሎ ተናገረ በሩቅ ስላለሁ ይሁን ማይክ ስላልተጠቀመ ብዙ ንግግሩ አልተሰማኝም ። ብቻ ፕሮግራም መሪው ከተናገረ በኋላ አስተማሪው እየሮጠ ማለት በሚቻል መልኩ ከመድረኩ ስር ተንበርክኮ ጌታ ኢየሱስ ፣ ጌታ ኢየሱስ ፣ ጌታ ኢየሱስ ፣ ጌታ ኢየሱስ ፣ ጌታ ኢየሱስ ፣ ጌታ ኢየሱስ እያሉ በተደጋጋሚ ይጣራሉ ፤ ከተንበረከኩበት አንገታቸው ብቻ ብቅ ሲያረጉ ፂማቸው ሂና የተቀቡ ሙስሊም የሚመስሉ ሰው ናቸው ። ጉባኤ ፊታቸውን ሲያይ ይሔ ሙስሊም ሰውዬ ምን ያህል ቢነካ የሚል አስተያየት ሳያያቸው አይቀርም ። ጉባኤው በሞላ አብረን በአንድነት በእንባ ጌታ ኢየሱስ እያልን ከልብ ስሙን ጠራን ።  ያስተማሩት ትምህርት አንጀት ቢያርስም የማረሳው ግን በተደጋጋሚ የተናገሩት ብዙ ጊዜ ይሔን ኢየሱስ የሚለውን ስም የመጥራት ልማድ የለንም !! በቻላችሁት መጠን ልክ ጥሩት ፣ ከሚያስደንቁ ልምምዶች  መካከል ዋነኛው ስሙን በቻላችሁት መጠን ከመረዳት ጋር ፣ ከመወደድ ጋር ፣ ከልብ ከሆነ ፍላጎት ፣ በስሙ ውስጥ ያለው መንፈሳዊ ሚስጥር ከመረዳት በመጀመር ኢየሱስ የሚለውን ስም  መጥራት ።

ከወር በኋላ የወንድሜን የህክምና ውጤት ዶክተር አረዳኝ ። እንዲሁ በቀላሉ ካንሰር ሲል የሰማሁትን እውነት መቋቋም አልቻልኩም ። ወንድሜ ሳያየኝ በዛው ሆስፒታል በመታጠቢያ ክፍል ውስጥ ረጅም ደቂቃዎች አለቀስኩ ። በቀላሉ የምቋቋመው አልነበረም ከቤተሰብ ተለይቼ የዛኑ ቀን ወደ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ነው የማድረው በማለት በእግሬ ረጅም መንገድ ሄድኩ ። መንገድ ላይ ለመፀለይ ሞከርኩ አልቻልኩም ። ለመጮኸ መኮርኩ አልቻልኩ ፣ ለማውራት ሰው ፈለኩ የቅርቤ የምላቸው እንኳን የሌለኝ መሰለኝ  ።

በመንገድ ላይ እያለሁ ከወር በፊት በጉባኤው ውስጥ ጌታ ኢየሱስ ብለን ከልብ በሆነ ናፍቆት ቅዱስ ስሙን የጠራንበት ጊዜ ትዝ አለኝ ። ከዛም እንዲህ እያልኩ መንገድ ላይ መፀለይ ጀመርኩ
  "የራሴ ድምፅ ብዙ ጊዜ ረበሽኝ ፣ እኔነቴ ያለ ቅጥ  መፈናፋኛ አሳጣኝ ፣ ድካሜ ጉልበቴን ለግሞ ያዘኝ ፣ የምሰማው ነገር አስደነገጥ  በዚህ ሁሉ ግን ስምህ መማፀኛ ግንብ ሆነኝ ። በዙሪያ ካሉት ሁሉ ዘልዮ አመለጥኩበት ። ቃላት አጥቼ ጌታ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ እያለኩ ለማምለጥ ጠራሁት ነገር ግን ማምለጡን ረስቼ የጠራሁት ስምህ ጣፈጠኝ ጌታ ኢየሱስ ብዬ ሳልጨርስ ከእንደገና ስሙን መጥራት ናፈቀኝ ። ጌታ ኢየሱስ ስለው የተወጋው ጎኑ ትውስ ይላል፣ጌታ ኢየሱስ ስለው የፈሰሰው ደሙ እንደ ወንዝ ጅረት በአይነ ህሊናዬ እልፍ ይላል፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው በመስቀል እንደ ተንጠለጠ ወድሃለው ሲለኝ ይሰማኛል ፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው ልክ በሌለው ጭንቀቴ ውስጥ ልክ የሌለው ሰላሙ ይፈሳል፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው ሀዘን ጥላውን ባጠላብኝ ነፍሴ ውስጥ ደስታው እንደ ማለዳ ፀሀይ ይፈነጥቅብኛል ፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው በውስጤ ያለው ቅዱሱ መንፈስ ደግሜ እንድጠራው ጉልበት ይሆነኛል ።  ሰሞኑን ብዙ ተጨነኩ ፣ ብዙ አዘንኩ ፣ብዙ አነባሁ ፣ ብዙ ተልፈሰፈስኩ እና ብዙ ብዙ ልል አስቤ ልፀልይ ተንበረከኩ ጌታ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ብዬ ስጣራ በአንድ ቃል ብዙ ተነፈስኩ ፣ አረፍኩ ፣ እፎይይ አልኩ !! "

       ጌታ ኢየሱስ😍



✍ ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd

🔥 14
🥰 9
❤ 4

በመፀሀፍ ቅዱስ ውስጥ የጠፋውን ልጅ ታሪክ ስናነብ በጣም የሚደንቀን የጠፋውን ልጅ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው የአባቱ ልብ ነው ። የአባትነትን ልብ ያየንበት ግሩም ታሪክ ነው ። ነገር ግን አባትዬው እጅግ ደስ የሚለው ጉዳይ ቤት ያለው ያልጠፋው ልጅ አለመጥፋት ብቻ ሳይሆን የጠፋውን ልጅን ያልጠፋው ልጅ አፈላልጎ እንዲያገኝ እና ወደ አባቱ ቤት እንዲመለስ አባቱ በብርቱ ይፈልጋል ። ቤት ያለው ልጅ የአባቱን ልብ አላገኘም ነበር ፤ ቤት ተቀምጦ ከአባቱ ልብ ርቋል ። ኢየሱስ ግን ከዙፋን ፣ ከሰማይ ድረስ የአባቱን ልብ ተረድቶ በበረት ተኝቶ ፣ በሰው መንደር አድጎ ፣ በመስቀል ላይ ውሎ ፣ በመቃብር ውስጥ አድሮ የጠፋውን የሰው ልጅ ፈልጎ አፈላልጎ አገኘ ። የአባት ልብ መረዳት እንዴት ደስ ይላል !! በኢየሱስ በኩል የተገለጠ የአብ ልብ አለ ። የአብን የልብ ሀሳብ ለመረዳት የፈለገ ማንም ቢኖር የአብን ልብ ባረካው በኢየሱስ በኩል ይገኛል ።  አብ በልጁ ኢየሱስ የልቡ ስለደረሰ እሱን ስሙት ብሎ የልብ የልቡን በኢየሱስ በኩል ተናግሯል ። 

@cgfsd
@ownkin

❤ 22
👏 2
🔥 1

መውደዱ በሥጋው መቈረስ ደመቀ፤ ለእኛ ያለው ፍቅሩ በደሙ መፍሰስ ታተመ። በቍስሉ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ተጨባበጥን። በሰማይ ለእግዚአብሔር ክብር፥ በምድር ለሰው ልጅ ሥምረት ኾነ (ሉቃ. 2፥14)። እነሆ፥ ዐዲስ የወዳጅነት መንገድ ተከፈተ። ከእግዚአብሔርም ጋር ኾነ ከሰው ጋር እንታረቅ ዘንድ መድኀኒት በቀራንዮ ተቈረሰ። ድኅነት ታወጀ። ኀጢአት ተሰረየ፤ የቀደመች ኀጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ተተወች፤ ዐመፃ ተጨረሰ፤ የዘላለም ጽድቅ ገባ፤ ምሕረት ተበሠረ፤ ፍቅር በመስቀል ላይ ሠመረ። በትንሣኤው ኀይል ጨለማ ድል ተነሣ፤ ለእግዚአብሔር ክብር ለሰውም ሰላም ኾነ።

                     ሰሎሞን አበበ ገብመድኅን

@cgfsd
@ownkin

🥰 11
🔥 2

Найдено 571 пост