Поиск по каналам Каналы в закладках Мои каналы Поиск постов
Инструменты
Мониторинг упоминаний Детальная статистика Анализ аудитории Telegraph-статьи Бот аналитики
Полезная информация
Инструкция Telemetr Документация к API Чат Telemetr
Полезные сервисы
Защита от накрутки Создать своего бота Продать/Купить канал Монетизация

Телеграм канал «በክርስቶስ ( in christ)»

በክርስቶስ ( in christ)
738
340
3
0
8.0K
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Подписчики
Всего
1 170
Сегодня
-1
Просмотров на пост
Всего
288
ER
Общий
24.94%
Суточный
22%
Динамика публикаций
Telemetr - сервис глубокой аналитики
телеграм-каналов
Получите подробную информацию о каждом канале
Отберите самые эффективные каналы для
рекламных размещений, по приросту подписчиков,
ER, количеству просмотров на пост и другим метрикам
Анализируйте рекламные посты
и креативы
Узнайте какие посты лучше сработали,
а какие хуже, даже если их давно удалили
Оценивайте эффективность тематики и контента
Узнайте, какую тематику лучше не рекламировать
на канале, а какая зайдет на ура
Попробовать бесплатно
Показано 7 из 738 постов
Смотреть все посты
Пост от 03.07.2025 15:08
18
0
0
( የክርስቶስ ፍቅር የነካቸው አባት) በዘላለማዊ የክርስቶስ ፍቅር ልባቸው የቀለጠው አባባ ዋንዳር ከትውልድ ስፍራቸው ሑምቦ እስከ ሶዶ ድረስ ገበያ አይቀር መንደሮች እየገቡ ወንጌል ይመሰክራሉ ። እሁድ  የአምልኮ መርሃ ግብር ወደሚደረግበት ሚስዮናዊያን ወደሚገኙበት ኦቶና ወላይታ ሲመጡ ከሑምቦ እስከ ወላይታ ባለው መንገድ ብዙ ሰው ወንጌል መስክረው የቅዳሜ ገበያ የሚጓዙ ሰዎች ይመስል ወደ ጣቢያው በገፍ ይዘው ይመጡ ነበር ። አባባ ወንጌልን በመቀበላቸው እየተክተለተለ የመጣባቸው እልፍ መከራ ነበረባቸው ። ልጃቸውና አባታቸው በጠና ይታመማሉ ። ለባህላዊ ለአምልኮ ለሚደረግለት  ግብር ስላቆምክ ነው እባክህን ለልጅህና ለአባት ስትል መስዋዕቱ አስቀጥል የሚል ምክር በተደጋጋሚ ይቸራቸዋል ።  ልጃቸውም ሆነ አባታቸው አረፉ በዚህ ምክኒያት ለራሱ ያልሆነ ብለው መጀመሪያ ሚስታቸውን ፣ ጓደኞቹን ፣ የገዛ ዘመዱ ትተውት ከእሳቸው ተለዩ ። በራሳቸውም የህይወታቸውን ፍሬ የተመለከቱት ባለቤታቸው ቆይተው ተመለሱ ። መከራው ግን የማያቋርጥ እየሆነ በእየጊዜ ግርፋቱ እየበረታባቸው መጣ ። ወቅቱ ጣሊያን ኢትዮጲያን የወረረበት ወቅት በመሆኑ ጣሊያን ሚስዮናዊያን ከሀገር አባረራቸው ። ሚስዮናዊያን ከተባረሩ በኋላ ራሱ ስደት ቢበረታም አባባ ዋንዳሮ የበለጠ አብዝተው በመላው ወላይታ ወንጌል ማዳረስ ቀጠሉበት ። ይሔን ጊዜ የአካባቢ ገዚ የነበረው ፊት አውራሪ ዶጊሶ በጣሊያኖች የሚስዮናዊያን ትምህርት አንዳይዛመት ጥበቃ እንዲደረግ በጥብቅ ትዕዛዝ ወጥቶ ተነግሯቸው ነበር ። አባባ ዋንዳሮን ፊት  አውራሪው አስጠርተው ። እምነትህን ካድ ካለበለዚያ የሚደርስብን ሀላፊነት አንወስድም አሉት ። አባባ ዋንዳሮም በምላሻው ላዳነኝ ጌታ በደስታ የመጣውን ሁሉ እንደሚቀበሉ በቆራጥነት ተናገሩ ።  ፊት አውራሪውም መልሰው ይሔን ድፍረት ልበ ሙሉነት ከየት ነው ያመጣኸው? ሚስዮናዊያን እንደሆኑ ዳግም ላይመጡ ተባረዋል ብለው ተስፋቸው የትም እንደማያደርሳቸው ነገሯቸው ።  አባባም ለመጨረሻ ጊዜ አስረግጠው ሚስዮናዊያን ብለው ሳይሆን የጌታን መንገድ ለመከተል የወሰኑ ያዳናቸውን ክርስቶስ ብለው እንደሆነ በወኔ ለመጨረሻ ጊዜ መለሱ ። ፊት አውራሪውም በንዴት ገበያ መሃል ህዝብ ሁሉ እያያቸው በሆዳቸው ተኝተው በገራፊውች በጠራራ ፀሃይ እንዲገረፉ ተወሰነባቸው ። አባባ መገረፍ የብዙ ጊዜ ተግባራቸው ነበር ። ሰውነታቸው በሰንበርና በቀስል በተበላሸ ቆዳ ፣ በረገፉ ጥርሶች ገፅታቸው የተሞላ ነበር ። አንድ ቀን በአባባ ዋንዳሮ ከሚማሩ ትጉህ አማኞች መካከል የሚያስታውሱት ትውስታ ሲናገሩ ። ቅዳሜ ቀን በነጭ ያሸበረቀ ልብሳቸውና የደረቡት ጋቢያቸውን ገቢያ መሃል እያንከባለሉ ሰረግጧቸው ሲገርፏቸው ዋሉ ።  አሁድ ቀን በቀይ አፈርና በደም ልብሳቸው ተጨማልቆ እሁድ ማለዳ ጉባኤውን ለማስተማር ተገኙ ። ጥቂት የነበሩን አማኞች ሲሰብኩ በእሁድ ማለዳ ልብሳቸው ተቀዳዶ የሰውነታቸውም ቁስሉ ይታይ ነበር ። አባባ በትውልድ ስፍራቸው ሑምቦ የፀሎት ቤት ሰርተው ነበር ። በዛም በርካታ አማኝ እየጨመረ እየበዛ በመሄዱ በሃይማኖት መሪዎችና በአካባቢ ገዚዎች ክስ ይቀርብባቸዋል ። በሑምቦ ያለውን የፀሎት ቤት አፍርሰው ፍርስራሽ ማቴሪያሎችን ተሸክመው ከሁምቦ ወላይታ እንዲያመጡ ትዕዛዝ ደረሳቸው ። አባባ ውሳኔው በፀጋ ተቀብለው ። አማኞች ጋር በደስታ እየዘመሩ የፀሎት ቤታቸውን አፍርሰው ከ25 የሚበልጥ ኪሎ ሜትር ተሸክመው በከፍተኛ ደስታ የአምልኮ ልብ ኢየሱስ ይመጣል መልስ ይሰጠናል እያሉ ከሑምቦ ወላይታ ድረስ አድርሰው እየዘመሩ ተመለሱ ። ከዛም በኋላ መሰባሰቢያ ስፍራ ስላልነበራቸው በእ የቤቱና በእየ ዛፍ ስር አምልኳቸውን ማረግ ቀጠሉ ። ሚስዮናዊያን ከወጡ በኋላ ትልቁ ስጋት የነበረው አማኞች ደቀመዝሙር የሚያደርግ ሰው ነበር ። ሚስዮናዊያን ጓዛቸውን ጠቅለለው ሲወጡ በቁጥር 48 የሚሆኑ አማኞች በወላይታ ይገኙ ነበር ምን ይሆናሉ በሚል ስጋት ተውጠው ወደ ሀገራቸው ሄዱ ። ጣሊያን ከሀገር ከወጣ በኋላ ሚስዮናዊያን እንዲመለሱ ሲፈቀድላቸው በፈርሃት ያሉት አማኞች ከምን ደረሱ ብለው ፈራ ተባ እያሉ ቢመጡ ያገኙት በተቃራኒው ነበር ። እነ አባባ ዋንዳሮ በቁስል ተሸፍነዋል ። 48 የሚሆኑ አማኞች በቁጥር 10,000 ደርሰው ጠበቋቸው ። ለዚህም ከባድ ወራቶች እነ አባባ ዋንዳሮ ለወንጌል በመጋደል ነበር የቆየት ። የሚድኑት ዕለት ዕለት ይጨመር የሚለው ቃል ተፈፀመባቸው ። ጣሊያን ሲወጣ መከራው ይቀንሳል ተብሎ ቢታሰብ የበለጠ እየጨመረ መልኩን እየቀየረ አስቸገራቸው ። አንድ ጊዜ ሁለት ወጣቶች መሃል ታሰሩ ። ወጣቶቹ ስቃዩ ሲበዛባቸው አባባ ምን ተሻለ ብለው ጠየቋቸው ። አባባም የሚሻላችሁ የኢየሱስ አዳኝ መቀበል ብለው እስር ላይ ባሉበት አዳኝነት አስተጋቡ ። እንደ አድባር ነገር ባለ የዛፍ ጥላ ስር ተቀምጠው ልጆችን ሰብስበው ፊደል ያስቆጥሩ መፀሀፍ ቅዱስ ያስተምሩ ነበር ።  በፈረስ እንዲሄዱ ፈረስ ቢገዛላቸው አሻፈረኝ አሉ ምክኒያቱም ደግሞ በፈረስ ስሄድ ሰው አላገኝም ስለዚህ ወንጌል መመስከር ስለማልችል አልሄድም በማለት እምቢታቸውን ገለጠ ። ስለራሳቸው ሆነ ስለደረሰባቸው መከራ ማውራት ብዙ የማይቀናቸው ። ስለ መከራው አውሩ ሲባሉ በክርስቶስ ስለተገኘው እርቅ መንገድ ያለመታከት ይናገራሉ ። በተለይም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የተገኘውን እርቅ አጉልተው ያሳያሉ ። ከመስበክ ባለፈ ህዝቡ በተግባራዊ ህይወቱ እንዲተገብረው የትንሳኤን መታሰቢያ ሰሞን ያላቸውን በሬ አርደው ቅዱሳኑን በማብላት ለእርቅ ትልቅ ስፍራ እንዲኖራቸው ለአማኞች ተምሳሌታዊ ባህሪያቸው ያካፍላሉ ። ምንጭ :- በመከራ ውስጥ ያበበች ቤተክርስቲያን        - WWW. Teachers essentials        - alittle about ababa wandaro(documentary) @cgfsd
Пост от 02.07.2025 14:10
8
0
0
ሰው ለብሔሩ ፣ ለቋንቋ በሚዋደቅባት አለም ውስጥ የሌላውን ቋንቋና ባህል ለወንጌል ለማወል የሚራብና የሚናፍቅ ፀጋ የረዳው ነው ። ክርስትና ውስጥ የራስ አጥር አልተፈቀደም ! ቋንቋ የእኔነት አባዜ ለማርካት ሳይሆን የክርስቶስ በላይነት ለመዘከር ይውላል ። ከሰፈር መውጣት አንዱ የክርስትና ባህሪ ነው ። ከራስ ባህል ፣ ቋንቋ አልፈን በሌሎች ቋንቋና ባህል ክርስቶስ ለማካፈል መናፍቅ የአማኝ ክብሩ ነው ። @cgfsd
Изображение
Пост от 01.07.2025 21:10
17
0
0
የመፀሀፍ ቅዱስ ጥናታችን አሁን ተጀምሯል
Пост от 01.07.2025 08:58
8
0
0
በወንጌል ያልተደረሰ ህዝብ አለመደረሱ ለክርስቲያን የልቡ ህመም ምክኒያት ነው ። @cgfsd
Изображение
Пост от 01.07.2025 07:27
18
0
0
ዛሬ ማክሰኞ ማታ 3 ሰአት በቴሌግራም ቻናል ኦላይን ላይ የምናጠናው የማቴዎስ ወንጌል የተራራው ስብከት ጥናታችን የሚሆነው ማቴዎስ 5:16 ላይ ይሆናል። እንደዚሁም ሰዎች መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰዎች ፊት ይብራ። ማቴዎስ 5:16 @cgfsd
Изображение
Пост от 30.06.2025 12:48
4
0
0
https://youtu.be/zugi3LghBxE?si=WB_IrdU4RoI8sFNm
Пост от 25.06.2025 10:18
12
0
0
(የአንድ ለአንድ ኢየሱስ) ኢየሱስ እልፍ አዕላፍ ተከትውታል ።አንዳንዶች ያጋፉትም ነበር ። ለህዝብ ፍቅር የነበረው ቢሆንም አንድ ሰው ቢሆን እንኳን አይንቅም ለማንም ትኩረት አይነፍግም ። የአንድ ሰው ጉዳይ በእርሱ ዘንድ የልብ ምት ነው ።  አንዳንድ ሚስጥሮች ለማውራት እስቲ ሰው ሰብሰብ በርከት ይበሉ ብሎ አዳማቂ አይሻም ።  2 አሳ እና 5 እንጀራን ሲያበዛ 5000 ሰዎች ከእሱ ተምረዋል ነገር ግን አንዳንድ እውነቶች የሰው ብዛት አይቶ አያወራም ።1 ሰው ቢሆን ልቡን ለማካፈል ዝግጁ ነበር ። መንግስተ ሰማያት ዳግመኛ ካልተወለደ አትገባም (ዩሀ3) ብሎ ያወራውን ሚስጥር በህዝብ ጋጋታ መሃል አልተናገረም ። በእውነትና በመንፈስ ነው የምመለከው በማለት ትልቅ መንፈሳዊ እውነት ከተማ ሲሰበሰብ አላወራም አንድ ሰው የሌላት የተገለለች ሰማራዊት ሴት ፊት ግን ተናገረ ። በብዙ ግፊያ ውስጥ አንድ ሰው በእርግጥ ነክቶኛል ብሎ ለመቆም የአንድ ሰው ጉዳይ አይቀልበትም ። ከሙታን ሲነሳ ስትጠባበቀው የነበረችውን መቅደላዊት ማርያም ለመታየት አይ ሰው ጠርቀም ይበልና አንድ ላይ እታያቸዋለሁ አይልም ለአንድም ሰው ቢሆን ዝቅ ማለት ልማዱ ነው ። ፈሪሳዊም ይሁን ቀራጭ ፈልጎ አንድ ለአንድ ለማግኘት ይሄዳል ። ፈሪሳዊው ስምኦን ቤት ለመገኘት አይከብደውም ።  ቀራጩ ዘኪዮስ ቤት ውስጥ ድረስ ዘልቆ ገብቶ የጠፋውን የሰው ልጅ ልፈልግ መጣሁ ይላል ። ህፃናትም ቢሆኑ ወደ እኔ ይመጡ አትከልክሏቸው ብሎ ይዳስሳል ። አይደለም የታመመን ለምፃምን የነካ በሚጠየቅበት የህግ ማህበረሰብ ዘንድ መካከል መንፃት ወዳለሁ ላለ ለምፅ ላለበት ምስኪን ፈውሱን ብቻ ሳይሆን አለሁልህ በሚል ልብ ቆዳው ይዳስሳል ። የዳዊት ልጅ ማረኝ እያለ ዝም በል እስኪባል ድረስ እየጮኸ ላለ ሰው ይምጣ ብሎ ይቆማል ። በመስቀል ሲቃ እያቃሰተ እንደተንጠለጠለ እናቱን ለደቀመዝሙሩ አደራ ይላል ። በኢየሱስ አገልግሎት ውስጥ አንድ ለአንድ የተባለ የአገልግሎት አይነት አለ ። ሰውን ለመስማት ፣ ለመረዳት ፣ ለማገዝ ፣ ለማቅረብ ፣ ወገን እንዳለው እንዲሰማ የማረግ አቅም አለው አንድ ለአንድ ሰው የመቅረብ መንገድ ። ኢየሱስ ደቀመዝሙር ለማድረግ ከተጠቀመባቸው ውጤታማ ዘዴዎች ውስጥ አንድ ለአንድ  መንገድ ነው ። @cgfsd  
Смотреть все посты